Monday, 16 December 2013

የኦሮሞ ጥያቄዎች ድሮና ዘንድሮ በጨረፍታ

የኦሮሞ ጥያቄዎች ድሮና ዘንድሮ በጨረፍታ
የኦሮሞ ጉዳይ ስነሳ ለምትደነግጡ ሁሉ ገና እልፍ አእላፋት ጊዜ እልፍ አእላፋት የኦሮሞ ጉዳዮች ስለምነሱ አትደንግጡ! ድንጋጤው በዚህ ከቀጠለ ተናችሁ ሁሉ ልታልቁ ነዋ!!! “በቁቤ” አይደለም፤ “በላትን አልፋቤትም” አይደለም የኦሮሞን ጉዳይ በራሳችሁ ፊደል ልናንፀባርቅባችሁ ነው፡፡ ቅንና በጎ አሳቢ ከሆነችሁ ጨረሩ አይጎዳችሁም፡፡ ድብቅ አጀንዳ ካላችሁና የኦሮሞን ጉዳይ የምትፈሩና ኦሮሞን እንደ ስጋት ምንጭ የምታዩ ከሆነ በፊደላችሁ ወደ እናንተ የምናንፀባርቃት የኦሮሞ ጉዳይ ጨረር ሆነ ልታነስራችሁ ትእላለች!!! 

ግን ኦሮሞን ለምንድነው እንደስጋት ምንጭ የምታዩት??? የምሬን ነው እኮ!!! ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን ያው ኦሮሞ መይም ኦሮሚያን የተመለከተ ነገር ስነሰ ሁሉም ፊቱ ይጠቁራል፡፡ እውነት ኦሮሞና ኦሮሚያ ክፉ ሆነው ነው ወይ? አይደለም!!! እናንተም አስረግጣችሁ ታውቃላችሁ…ግን የኦሮሚያና ኦሮሞ ጉዳይ ስነሳ ሰዉ እንዲህ ፊት የምከሰክስበትና በፍርሃት የመናጥበት የሆነ የተደበቀ ምስጥር እንደለ ይሰማኛል፡፡ ማንነት ከሆነ ማንነት ማንነት ነው ለምን የሌላ ብሄርና ብሄረሰብ የማንነት ጉዳይ ስየሳ ሰዉ ብዙም አይጨነቅም? የኦሮሞ ሲሆን ጠባብ፡ ዘረኛ፡ ፀረ-ኢትዮጵያ ወዘተ በዘመቻ መትመም ለምንድነው? የሆነ ከድሮ ጀምሮ አሁንም የምትፈሩ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ይሄ ድሮም ነበረ አሁንም ያለ ትልቁ ችግር ነው፡፡

ቆይ ቆይ…የኦሮሞ ጥያቄ ተመልሷል ብላችሁ ልትሸውዱን የምትሞክሩ ባለተረኞች የኦሮሞ ጥያቄ በቋንቋው የመናገር መብት ብቻ ነው እንዴ? የድሮዎቹ ቋንቋችንና ባህላችንን ጭምር ልነፍጉን ሞከሩ፡፡ ማንነታችንን ለመሰረዝ ሁላ ደነፉብን፡፡ በዚህ መሃል ስንትና ስንት ግፍ ተፈፀብን፡፡ ትልቁን መዘውር ኢኮኖሚውንና ፖሊትካውንም ጠቅልለው ያዙና በገዛ ቤታችን የበይ ተመልካች አደረጉን፡፡ የዛሬዎቹ ባለተረኞቹ መጡና ቆምንለት ያሉት አላማ እንደሽፋን ይዘው ባለተረኞች ሆኑብን፡፡ ቋንቋችሁን፤ ባህላችሁን አንድታሳድጉ ዕድል ተሰቷችኋል አሉን፡፡ ጥሩ አልናቸው!!! ግን ሌላ ብዙ ጥያቄዎች አሉን አልናቸው፡፡ ጀመርን…የእጃዙር ጉዞ አይመቸንም ኣልናቸው፡፡ ኦሮሚያና ኦሮሞ ከኢኮኖሚው በሚገባው መጠን መጠቀም ግዴታ መሆኑን አቋማችን መሆኑን አስረግጠን ነገርናቸው፡፡ ስልታዊ መሰርሰርና በእጃዙር መበዝበዝ እያንገሸገሸን ነው ኣልናቸው፡፡ በፖሊትካም ስልጣን ቢሆን አንዱ አድራጊ ፈጠሪ አንዱ ጉዳይ አሰፈፃሚ ሆኖ መጓዙ እስከመቼ ይቀጥላል ብለን ትልቅ ቅሬታ እንዳለን ነአደባባይ ተናገርን? ለዚያውም ለዚህች ሀገር ህልውና ትልቁን እያበረከትን!!!! ከዚያም “በፀረ” የምጀምሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ቃለት ለጠፉብን!!! 

እናማ አንድና አንድ ነገር እንነጋገር….ኦሮሞ ፍትሃዊነት ካለ በኢትዮጵያ ጥላ ስር መቀጠል ችግሩ አይደለም፡፡ በፊት ከነበረውና አሁን ካለው ዓይነት የተሻለ ሁኔታ እንፍጠር ከተባለ በሩ ዝግ አይደለም፡፡ መቼም ዝግ አያደርግምም!!! ግን ሰዉ አጉል ብልጥነት ስሞክርና ኢፍትሃዊነት ስነግስ ዕዳ ኣለብን አንዴ ሁላ ያስብላል!!!///

No comments:

Post a Comment