Saturday, 11 January 2014

የቀድሞው የእስራኤል ጠ/ሚ/ር በ85 ዓመታቸው ሕይወታቸው አለፈ



(ዘ-ሐበሻ) የቀድሞው የ እስራኤል ጠ/ሚ/ር ኤራል ሻሮን በ85 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉን የሃገሪቱ ሚዲያዎች ዘገቡ።
ከ2006 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በሞት እና በሽረት መካከል ሕይወታቸው የቆየችው እኚሁ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሕይወታቸው ያለፈው በስትሮክ በሽታ ነው። የሰውነታችን አጠቃላይ አዛዥና ተቆጣጣሪ በሆነው አንጐላችን ላይ በድንገት ተከስቶ ለአካል ጉዳተኛነትና ለሞት የሚዳርገው ስትሮክ፣ ዛሬ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዓለማችን ህዝቦች አሳሳቢ የጤና ችግር መሆኑን በዘ-ሐበሻ የጤና አምዶች በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
የሼባ ሜዲካል ሴንተር ቃል አቀባይ ሲሞ ኖይ ለሚዲያዎች “ኤሪያል ሻሮን አርፏል” በሚል ከቴል አቪቭ ዛሬ ቅዳሜ ማረጋገጫ እንደሰጡ ዜናውን በሰዓታት ውስጥ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።
የ እስራኤል 11ኛው ጠ/ሚ/ር የነበሩት ሻሮን በአውሮፓውያን አቆጣጠር ከማርች 2001 እስከ ኤፕሪል 2006 ዓ.ም እስራኤልን በጠ/ሚ/ርነት አገልግለዋል። ከዛ በፊት ቤንጃሚን ኔታንያሁ እስራኤልን በጠ/ሚ/ርነት በሚመሩበት ወቅት በውጭ ጉዳይ ሚ/ርነት ለአንድ ዓመት አገልግለዋል።


ፌብሩዋሪ 26 ቀን 1928 የተወለዱት ሻሮን የ3 ልጆች አባት ነበሩ።

No comments:

Post a Comment