Monday, 24 February 2014

ወጣቱ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ

ጽዮን ግርማ

በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
 (ሰኞ የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 24, 2014)፦ ዛሬ በምሳ ሰዓት አካባቢ፤ በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ”ኑሮ መሮኛል” ሲል ተሰምቷል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻውቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ (እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል።
በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል። የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን፤ አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል። የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው

No comments:

Post a Comment