ከተመሰረተ ከ70 ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ዛሬ ቃጠሎ እንደደረሰበት ወኪላችን ከአዲስ አበባ ዘገበ።
የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት የቃጠሎ መንስኤ ለጊዜው በዝርዝር ባይገለፅም በማተሚያ ቤቱ ላይ እሳቱ የተነሳው ከቀኑ 9 ሠዓት ተኩል ግድም እንደሆነ የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ከአካባቢው ነዋሪዎች ያገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ ገልፆልናል። እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተነግሯል። የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት በዕድሜ ጠገብነቱ እና ግዝፈቱ በሀገሪቱ ብቸኛው የማተሚያ ቤት እንደሆነ ይጠቀሳል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ
No comments:
Post a Comment