Sunday, 1 February 2015

አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን ተከናነቡ

አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን ተከናነቡ 

  • 12.2K
     
    Share
aba dula
በምሽትና በድብቅ ሀሙስ ምሽት ሚኒሶታ የገቡት የሕወሓት ተላላኪው ባለስልጣን አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን መከናነብ የጀመሩት ገና ከአውሮፕላን ከወረዱ ጀምሮ ነበር::
አባዱላ የሕወሓት ተላላኪ ሆነው የኢትዮጵያን እመራታለሁ እያሉ ከኤርፖርት የተቀበሏቸው ጥቂት ሶማሊያውያን የታክሲ ሾፌሮች ናቸው:: እነዚህ የሱማሊያ ታክሲ ሾፌሮች አባዱላን ከተቀበሉ በኋላ ብሎሚንገተን በተሰኘው የሚኒሶታ ከተማ ሂልተን ሆቴል ያሳረፏቸው ሲሆን እንደዚህ ቀደሙ የወያኔ ተላላኪዎች ሲመጡ ፖስተር ተለጥፎ ስብሰባ እንደሚጠራው ለአባዱላ የወያኔ ተላላኪዎች ያደረጉት ነገር የለም:: ይልቁንስ በቴክስት መልክት ብቻ በስልክ የወያኔ ኔትወርኮች ብቻ እንዲጠራሩ የተደረገና ሌላው ሕዝብ የአባዱላን ስብሰባ እንዳይሰማ ለማድረግ ጥረት ቢደረግም ይህ ቴክስት መልዕክት ለኦሮሞዎች  ደረሰ::
ኢትዮጵያውያኑ ልክ እንደሕወሓት ተላላኪዎች ድምፃቸውን ሳያሰሙ በቴክስት መልዕክት የተጠራሩ ሲሆን ስብሰባው የሚደረግበት ሂልተን ሆቴል ተገኝተዋል:: አባዱላ ገመዳ ከአንዲት ሴት ጋር ሁለተኛ ፎቅ ላይ ቁጭ ብለው ወደታች በአንደኛው ፎቅ በኩል የሚገቡትን ሰው እየተመለከቱ; አጠገባቸው ያለችው የትግራይ ተወላጅ የሆነች ሴት የሰውን ማንነት የምትነግር ይመስል ለባለስልጣኑ ትጠቁማለች::
በዚህ መሃል  ሲገቡ ሴትየዋ ለአባዱላ በጥቆማ ስታሳይ  ተመልክተዋል:: የኦሮሞ የነፃነት ታጋዮች  ወደ ስብሰባው ሊገቡ ሲሉ እንደተለመደው የተከለከሉ ሲሆን ስብሰባውን ያዘጋጀው አካል ከ30 በላይ የሚቆጠሩ ፖሊሶችን በመቅጠር ተቃዋሚ የሆኑ ሰዎች እንዳይገቡ ተከልክለዋል:: አንድ ፖሊስን በሚኒሶታ ለአንድ ዝግጅት በሰዓት መንግስት ከሚከፍለው በተጨማሪ ዝግጅት አዘጋጁ ከ$50 ዶላር ያላነሰ የሚከፍል ሲሆን የሕወሓት መንግስት ለነዚህ የአሜሪካ ፖሊሶች ለ6 ሰዓታት ለ እያንዳዳቸው $300 ዶላር በአጠቃላይም ለፖሊስ 9 ሺህ ዶላር አውጥቷል:: ይህም በኢትዮጵያ ብር ሲመነዝር 180 ሺህ ብር መሆኑ ነው:: ለአዳራሽ በትንሹ ከ2 ሺህ ዶላር በላይ, ለሶማሌ ታክሲ ሾፌሮች በሰዓት ከ60 ዶላር በላይ እንዲሁም ለአባዱላ እና ለተላላኪዎቻቸው የሆቴል አዳር ከ150 ዶላር በላይ የወጣበት ይኸው የሚኒሶታ ስብሰባ ካለስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን በስበባው የተገኘው ሕዝብም ከ45 ሰው እንደማይበልጥ በውስጥ ጉዳዩን እንዲከታተሉ የላክናቸው ምንጮች አስታውቀዋል::
የሕወሃት መንግስት ተላላኪው አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ስብሰባ እንዲያደርግ ግማሽ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ያጠፋ ሲሆን ያተረፈው ጥፋትን ብቻ ሳይሆን አባዱላ ገመዳ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ስድበንም ጭምር ነው:: በርከት ያሉ የኦሮሞ የነፃነት ታጋዮች  በሂልተን ሆቴልና በተለያዩ አባዱላ በሄዱባቸው የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች በመገኘት አባዱላን በሰብ አዊ መብት ረገጣ, በአፋኝነት, በአምባገነንነት, በሙስና እና በግድያ ወንጀሎች ሲናገሯቸውና በርሳቸው ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ሲያሰሙባቸው ውለዋል:: በአጠቃላይ የሕወሓት መንግስት የዲያስፖራ ሳምንት በኦሮሚያ አከብራለሁ ብሎ ስብሰባ የጠራበት የአባዱላ ስብሰባ ከትርፉ ኪሳራው አመዝኗል:: የኦሮሞ ነፃነት ታጋዮችም በሚኒሶታ በተቃውሞ ሲያሸብሩት ውለዋል::
አባዱላ ገመዳ ዛሬ በሚኒሶታ የደረሰባቸው ቅሌት ነገ በሲያትል እንደሚደገም ይጠበቃል:: በሲያትል ያሉ ኦሮሞዎች የአባዱላን የህወሃት ተልኮ ለማክሸፍ እየተጠባበቁ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

No comments:

Post a Comment