Thursday, 28 November 2013

እኔንጃ እስቲ ግን እናንተ መፍትሔው ምንድን ነው ትላላቹ ????

 
 


የሰው ሂወት ከዱር እንሰሳ ያነሰበት ጊዜ ዛሬ በሳውድ አረቢያ በፖሊስ መኪና ተገጭታ የሞተችው እህታችን  ትውልድ እንደ ቅጠል እየረየረገፈ ነው። ግማሹ በስደት ኑሮ አማሮት እራሱን ሲያጠፋ ፣ ገሚሱ በመኪና አደጋ ፣ ገሚሱ ኢሰባዊነት በጎደለው መንገድ በጎዳና ላይ ያለማንም ከልካይ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደል የተቀረው እንዲህ ያልፍልኛል ብሎ በሰው ሀገር ድፍት ይላል ። ምን ትል ይሆን ያልፍልኛል ብላ በስ ስት ልጇን በስደት ያጣች እናት???? ለሞቱት እግዚአብሔር ነብሳቸውን በገነት ያኑረው። ለወያኔም መንግስት ብድሩን እግዚአብሔር ይክፈለው።ሌላ የሚገርመው እንደ ተስፋዬ ጨመዳ አይነቱ ደግሞ ለህዝብ ሲል በእስር ቤት ተሰቃይቶ እዛው እስር ቤት ይሞታል። ያሳዝናል ከቤታቸው ልጆቻቸውን ጧሪ የሌላቸው እናት አባታቸውን ተነጥለው ከሃያ ሺ በላይ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ቀን ከለሊት እየተሰቃዩ ሞትን መጠባበቃቸውን ሳስብ መሪዎች ተብዬዎቹ ከሰው መፈጠራቸውን እጠራጠራለው። ግን ከሰው ነው የተፈጠሩት? እኔንጃ እስቲ ግን እናንተ መፍትሔው ምንድን ነው ትላላቹ ????  

No comments:

Post a Comment