Friday, 29 November 2013

ውግዘትና ሞት ለአምባገነን መንግስቶች ይሁን"!



ሶሴፕን እናግዝ
ፈይሳ አጽብሃ

ውግዘትና ሞት ለአምባገነን መንግስቶች ይሁንና ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ በተካሄዱት ኢሰበአዊ ድርጊቶች 
ሕይወታቸውን ለማትረፍ በአለም ዙሪያ የተሰደድነው ኢትይዮጵያውያን ቁጥር ባያሌ ሚሊዮን 
ተቆጥሩአል፡፡ በተለይ በወያኔ የግፍ ዘመን በመሰደድ ላይ ያለው ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየናረ ይገኛል፡፡ 
በረሃ ላይ የቀለጡት ላውሬ የተዳረጉት ውቅያኖስ የዋጣቸው በየኣሕጉራቱ እስርቤት የሚማቅቁት 
ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ ባገር ላይ ኑሮው አልተመቻቸው በውጭ አገር የያገሩ መንግስታትም ሆኑ ሕዝቡ 
መልካም አቀባበል ቀርቶ ሰብአዊ ርሕራሄም ነፍጎ ጭራሹኑ እያዋረድና እየገደላቸው ይገኛል፡፡ ባገር ውስጥ 
በየእስር ቤቱ የሚማቅቁና ታስረው ግን መዳረሻቸው የጠፋ በርካታ የፓለቲካ ሰዎች ለቤተሰባችወና 
ለድርጅታችው የዘላለም ሃዘን ሆነው ቀርተዋል፡፡ ግፉ ብዙና ተዘርዝሮ የሚያበቃ አይደለም፡፡ ለነዚህ ሁሉ 
ከሃያ አመታት በላይ ግንባር ቀደም ሆኖ በመቆም ያልታከተ ድምጽ ሆኖ በመታገል ላይ እንዳለ በየቀኑ 
የምናየው ሃቅ ነው፡፡ 
ማንኛውም አገርና ወገን ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በወገኑ ላይ ባገርቤትም ይሁን ካገር ውጭ የሚሰራበትን 
ግፍ ያወግዛል፡፡ የተበደሉትንም ለማገዝ ይጥራል፡፡ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ ይተደረገው 
ግፍ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን በየትም የአለም አካባቢ ያለውን ወገን አሳዝኗል፡፡ የዘመኑ 
ኤሌክትሮኖቲክ መገናኛ ያግዛልና ሕዝቡ በፍጥነትና በቀለጠፈ መንገድ ፈጥኖ ለመድረስ ይዘጋጃል፡፡ 
እርዳታውን የሚልክበት መንገድ ግን ገና ግልጽነት አላገኘም፡፡ የሕዝብን ሰቆቃ በመጠቀም ወይ ለግል 
ያለያም ለፓለቲካ ጥቅማቸው የሚሽቀዳደሙ ሰዎች ወይም አስመሳይ ድርጅቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ 
ሳይታለም የተፈታ ሕልም ነው፡፡ እንደ ሶሴፕ አይነት ድርጅቶች መኖራቸው የተደገፍ ቢሆንም ግን እንደ 
ሶሶአፕ የመሰለ ተመክሮ ጠገብና ሃቀኛ ድርጅት ግን መኖሩ አጠራጣሪ ነው፡፡ እስቲ ሶሴፕን ልዩና 
የሚያስመካ አገር በቀል የሰበአዊ መብት ተሟጋች የሚያደርጉትን ባሕሪያት እንደርድር፡ 

1. ከሃያ አመት በላይ ሰበአዊ መብታቸው ለተጣስ ስደተኞችና የፓለቲካ እስረኞች መብትን 
በተመለከተ ድምጽ ሆኖ እየታገለ ነው 

2. በረጅም ተመክሮው በርካት የአለም አቀፍ ሰበአዊ ድርጅቶችና ከአርጀንቲና፤ጉተማላ፤ ቺሌ፤ 
ፊሊፒን፤ ቻይና አፍጋኒስታን . . የሰበአዊ መብት ተከራካሪዎች ጋር ጠንካራ የስራ መረብ (ኔት 
ወርክ) የፈጠረ ድርጅት ነው 

3. ተቀባይነትና ተደማጭነትን በማትረፉ ስለ ስደተኛ ሰፈራ ጉዳይ ከካናዳ ከኖርዌና ከስውዲን የውጭ 
ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር የተነጋገረና ተግባራዊ ለማድረግ የጣረ ድርጅት ነው 

4. የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መብታቸውን በተመለከተ ለኬንያ ለደቡብ አፍሪካ ለሊቢያ ለሱዳን . . 
. መንግስታት ደብዳቤ በመጻፍ ስለ ዜጎቻችን መብት የቆመ ጠንካራ ድርጅት ነው 

5. በተለያዩ አገሮች በእስር ላይ የሚማቅቁትን ኢትዮጵያውያን ከታሰሩበት ስፍራ በመገኘት ጉብኝት 
ያደረግ ነው 
6. ሶሌፕ አለም አቀፋዊ ነውና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በሰሜን አሜሪካ በካናዳ በጀርመን
በስካንዲኔቪያና በአፍሪካ አሉት፡፡ ቅርንጫፍ በሌለበት ለመክፈት ይሞክራል 

7. በትግሉ በካናዳ ከአንድ መቶ ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን ማስፈር የቻለ ሃቀኛ ድርጅት ነው 

8. ላለፉት 20 አመታት በጥቂት ደጋፊዎቹ ርዳታ ብቻ ያለባጀት በመንቀሳቀስ ላይ ያለ አትራፊ 
ያልሆን ድርጅት ነው 

9. በአለም የመጀመሪያው በሆነውና በካናዳ በሚገኘው “አለም አቀፍ የሰበዊ መብት ተክራካሪዎችን 
ስራ ለኤግዚቢት በሚያሳየው ሙዚየም ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተሰሩትም ግፎች የሚያሳይ 
ስፍራ ያስገኘ ታዋቂ ድርጅት ነው 

10. በካናዳ ለለፉት ስምንት አመታት ከሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ሀ) ደዝባቸው 
ለጠፍ የፓለቲካ ሰዎች የሚዘጋጅ ምሽት ለ) ለእውነት ሩጥ የተባሉ ሕዝባዊ ዝግጅቶችን 
የሚዘጋጅና በርካታ ኢትዮጵያውያንንና የካናዳ ዜጎችን ማሰለፍ የቻለ ድርጅት ነው 

11. በቅርቡ ‘አንድ ሺ ኣንድ” የተባለ ፕሮጀክት በማዘጋጀት ማንኛውም ሰው ለፓለቲካ እስረኞች 
እንዲጽፍ ተደርጎ በመጽፋፍ መልክ ከተዘጋጀ በሁአላ መጽሃፉ ለፓለቲከኛ እስረኞች 
ለቤተሰባቸውና ለሕዝብ የሚበተን ታሪካው ስራ ያዘጋጀ 

እንግዲህ ይህን የተመክሮ ባለጸጋ የሆነ ያለበጀት ለረጅም አመታት በመንቀሳቀ ድምጽ ላጡት ድምጽ የሆነ 
ሃቀኛ ድጋፍ በማድረግ ወገኖቻችን ላይ በየአካባቢው የሚደረገውን ግፍ ለማስቆም መተባበሩ 
የማንኛውም አገርና ሕዝብ ወዳድ ዜጋ ግዳጅ ነው፡፡ ገንዘባችንንና ድጋፋችንን ለሃቀኛው ሶሴፕ ድርጅት 
እናውል

No comments:

Post a Comment