Friday 28 February 2014

Ethiopians return home to a bleak future


More than 150,000 Ethiopians have been deported from Saudi Arabia in recent months.

SONY DSC
Ahmed woke up in a Riyadh hospital with his kidney removed
March 1, 2014, Addis Ababa, Ethiopia (Aljazeera) - Ahmed, 20 years old, weakly sits down in a chair under the hot sun, dazed, as young men and women jostle in the yard around him. He has just been deported from Saudi Arabia after a month-long imprisonment, like the others at this crowded migrant transit center in Ethiopia’s capital.
But Ahmed’s ordeal is unique. He bears fresh scars across his knees, down his upper arms, and across his stomach. With a medical investigation by an Ethiopian doctor still ongoing, preliminary resultsshow so far that Ahmed is missing his left kidney.
His short-term memory fails him. Ahmed, who comes from Ethiopia’s central Amhara region, does remember paying a couple hundred dollars to human smugglers for the dangerous, illegal passage to Djibouti, across the sea to Yemen, and north to Saudi Arabia. 
He worked for a year and a half as a carpenter in Riyadh, living with other Ethiopian migrants and sending home meagre wages to his impoverished family.
Three months ago Ahmed recalls waking up in a Riyadh hospital room with jagged wounds crisscrossing his body, but with no recollection about how he got them, or how he got there. Promptly transferred to an overcrowded Riyadh prison because of his illegal immigration status, Ahmed was finally deported home by plane a few weeks ago. He is waiting to hear the doctor’s final prognosis before he returns to his village, a sickly version of his former self.
‘Coming back empty-handed’
saudideportees“It’s not just the return, it’s also the effect of what happens after,” explained Sara Hamo, a protection officer with the International Organisation of Migration (IOM) in Addis Ababa, about the thousands of deportees. ”They are coming back empty-handed. They used to supply money and now they are a burden on the families they used to provide for. So the return is just the beginning.”
While accounts like Ahmed’s missing kidney are rare, many Ethiopians at the migrant transit centre talked about torture in ad-hoc detention centres run by traffickers, most often for ransom, as well as beatings, sex abuse, gruelling work hours and wages withheld by Saudi employers.
Bereket Feleke, a health ministry official, said respiratory tract infections were the most common ailment returnees suffer, which they get from being held for weeks in overcrowded and filthy detention centres before deportation.
Ethiopian women and girls, often recruited by employment agencies as domestic workers, fly to Saudi Arabia and are legally bound to their employers, who withhold their passports. If the workers break their contract – willingly or forced - their status becomes illegal. A similar system of employee “sponsorship”, known askafala, exists across many of the Gulf states. But many more Ethiopian migrants in Saudi Arabia are smuggled in, further increasing their vulnerability for exploitation.
Travel ban
Because of widespread abuse, the Ethiopian government has issued a temporary travel ban on domestic workers while it works on a protection law. Critics say this could encourage more illegal migration.
Last November, the kingdom’s authorities enforced strict labour laws governing foreign workers after a seven-month reprieve, spurred partly by the potential security threat of thousands of unemployed Saudi youth. And Saudi Arabian vigilante groups in Riyadh, armed with clubs and machetes, brutally attacked Ethiopian migrants in November, prompting tens of thousands of the workers to turn themselves in to the kingdom’s authorities out of fear.
When I asked for payment, and permission to call my family, the man of the house said: ‘You have no family, so why do you need money?’ He tied my hands behind my back, put cloth in my mouth and beat me. He then kicked me out of the house.
Abigail, Ethiopian orphan
Unskilled labourers from neighbouring Yemen, the Horn of Africa and southeast Asia have been particularly hard-hit by the deportations, which the Saudi Arabian interior ministry claims have reached around a quarter of a million. Adam Coogle, a Middle East researcher with Human Rights Watch, suspects the number is much higher. ”I think workers from different nationalities are taking a wait-and-see approach to what is happening in Saudi Arabia,” Coogle said. “They will want to see if this is a labour crackdown that is sustained, or if it is just to scare them, and will end up being business as usual.”
IOM in Addis Ababa estimates that nearly 160,000 Ethiopians have been detained and deported from Saudi Arabia because of their irregular status. The peak was in November, when 9,000 deportees arrived on planes to the Ethiopian capital every day. These days, the numbers have dwindled to around 300 a day.
At nearly 92 million, Ethiopia has Africa’s second-largest population after Nigeria, and a rapidly growing economy. Agriculture is the country’s leading economic sector, but drought, poor cultivation practices, land-grabs and mass displacement of rural populations have garnered headlines recently. The youth unemployment rate is high. Many choose to seek work abroad and send remittances home.
‘They have been targeted’
Abigail is a 15-year-old orphan from an Amhara village who quit school when she was in the second grade. Her seven-month trip to Saudi Arabia was arduous. Her uncle paid an agency to find her work in the kingdom, and send money home. With her passport withheld, she cleaned and took care of the children in the household she was assigned to, as well as their relatives’ homes.
“When I asked for payment, and permission to call my family, the man of the house said: ‘You have no family, so why do you need money?’” she recalled. “He tied my hands behind my back, put cloth in my mouth and beat me. He then kicked me out of the house.”
The police arrested Abigail. Without her passport and valid working papers, she was imprisoned and deported. ”There is an anger within the Ethiopian population,” said Temesgen Deressa, a guest scholar with the Africa Growth Initiative at the Brookings Institute. ”They have been targeted - killed, or tortured and dehumanised.”
“In terms of the whole economy, the remittances might not be significant, but the returnees’ families are going to be hard-hit,” he said. “There is a high level of poverty in Ethiopia, and I don’t think the Ethiopian government has the capacity for rehabilitation. Basically, the returnees will have a very hard time.”
Source: Aljazeera

Wednesday 26 February 2014

ምነው ሚኒስትር ዘነቡ ?






ትናንት ማታ የሴቶች፣ ሕጻናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዘነቡ በትዊተር ገጻቸው ላይ ግብረ ሰዶምን
በተመለከተ የጻፉትን ነገር ከምመለከት ወይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባይኖር ወይ እርሳቸው ሚኒስትር ባይሆኑ
እመርጥ ነበር፡፡ የሴቶችና የወጣቶች፣ የሕጻናት ሚኒስትር ሆነው ግብረ ሰዶምን በመደገፍና የዑጋንዳን አዲሱን
ሕግ በመቃወም መጻፋቸው ‹‹ይህቺ ሀገር ወዴት እየሄደች ነው›› ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል፡፡ ከተወሰኑ ጊዜያት
በፊት በአዲስ አበባ የተሾሙ የአሜሪካ አምባሳደር በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያን መብት እንዲጠበቅ እሠራለሁ
ያሉትን አስታውሼ እኒህ ዲፕሎማት እውነትም ሠርተዋል ማለት ነው አልኩ፡፡
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት የኤች አይ ቪ ኤድስ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲደረግ የእምነት ተቋማት መሪዎች ግብረ
ሰዶምን በመቃወም መግለጫ ለመስጠት ተዘጋጅተው ወዲያው ነበር የተሠረዘው፡፡ ግብረ ሰዶማውያንን ተዋቸው
ተብለው መግለጫቸው መሠረዙ፣ እነርሱም ያንን በዝምታ ማለፋቸው በሀገራችን ከተከናወኑ አሳዛኝ ተግባራት
አንዱ ሆኖ እንዲመዘገብ አድርጎታል፡፡
ዑጋንዳ ሕጉን ያወጣችው የግብረ ሰዶማውያንን ተግባር ለመከታተል፣ ለመቆጣጠርና ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ
ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕግም ግብረ ሰዶም ወንጀል መሆኑን ከዑጋንዳ ቀድሞ የደነገገ ነው፡፡ ምነው ሚኒስትራችን
የግብረ ሰዶም ደጋፊ ሆነው ብቅ አሉ፡፡ ይህ ሕግኮ እርሳቸውንም የሚመለከት ነው፡፡ ግብረ ሰዶም በሀገሪቱ
በድብቅ እየተድፋፋ ሕጻናትና ወጣቶችን እየቀጠፈ፣ ማኅበረሰባዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችንን እያፈረሰ ነው፡፡
ሰውን ከተፈጠረበት ዓላማና ግብር ውጭ የሚያደርግ ነው ግብረ ሰዶም፡፡ እንስሳት እንኳን የማይፈጽሙትን
የሚያስደርግ ነው ግብረ ሰዶም፡፡
ምዕራባውያን በራሳቸው ምክንያት የተነሣ የዚህ ሐሳብ ደጋፊም አቀንቃኝም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነርሱ የደገፉትን
ሁሉ የመደገፍ ግዴታ ግን የለብንም፡፡ የእነርሱ ማኅበረሰባዊ ሥሪትና የእኛ ሥሪት ፈጽሞ አይገናኝም፡፡ በርግጥ
ይህንን መሰል ርካሽ ነገሮችን መደገፍና ማቀንቀን ዓለም ዐቀፍ ተቀባይነትን ለማግኘት አቋራጭ መንገድ መሆኑ
ይታወቃል፡፡ እኛ ግን ሚኒስትራችን የምንፈልጋቸው ለአሜሪካ ጉዳዮች አይደለም፤ ለኢትዮጵያ ጉዳዮች እንጂ፡፡
እርስዎ የተሾሙላቸው ሕጻናት፣ ሴቶችና ወጣቶች ሥራ፣ ንጹሕ ውኃ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የጤና ተቋማት፣ ሰብአዊና
ፖለቲካዊ መብቶች ቸግሯቸው እንጂ ግብረ ሰዶምነት አልቸገራቸውም፡፡ ግብረ ሰዶምነት የእነርሱ ማጥቂያ
መሣሪያ እንጂ ክብርት ሚኒስትሯ የሚቀኙለትና የሚሟገቱለት አይደለም፡፡
ለሕጻናት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች ያልተሠራ ብዙ አጀንዳ ባላት ሀገር፣ በዐቅም እጥረት በጤና ተቋማቱ የማይወልዱ
እናቶች፣ በየጉራንጉሩ የሚወለዱ ሕጻናት፣ በየጫት ቤቱ ሥራ ፈትተው የሚባዝኑ ወጣቶች ያሏት ሀገር ግብረ
ሰዶምን ጉዳዬ ብላ ማቀንቀኗ በዜጋ ላይ የሚፈጸም ስላቅ ነው የሚሆነው፡፡
እኔ ይህ መልእክት አሁንም የእርሳቸው ባይሆን እመርጣለሁ፡፡ ማብራሪያ እንደሚሰጡበትም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡


  ሚኒስትሯስ ምን ይላሉ? 
ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዘነቡ ለታድያስ አዲስ ዛሬ በ9 ሰዓት በሰጡት መግለጫ ‹‹ከልብ ነው ያዘንኩት፤ የእኔም አቋም
አይደለም፤ የመንግሥትም አቋም አይደለም፤ ያየሁትም በትናንትናው ዕለት ነው፤ በሆነውም ነገር በጣም ነው
ያዘንኩት፤ በተፈጠረው ነገር ሰብእናዬ ተጎድቷል፡፡ እስከ መጨረሻ ማጣራት ያለብኝን አጣራለሁ፡፡ ይህ በሀገሪቱ
ሕግ ላይ የተቀመጠ ወንጀል ነው፡፡ ከእኔ ሰብእናም ጋር አይሄድም›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች
ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስም ‹‹አካውንታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተጠልፏል›› ብለዋል፡፡

Monday 24 February 2014

ወጣቱ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ

ጽዮን ግርማ

በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
 (ሰኞ የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 24, 2014)፦ ዛሬ በምሳ ሰዓት አካባቢ፤ በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ”ኑሮ መሮኛል” ሲል ተሰምቷል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻውቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ (እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል።
በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል። የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን፤ አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል። የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው

Sunday 23 February 2014

ይድረስ የኦሮሞ ጥላቻ እና ፍራቻ (ኦሮሞ ፎብያ) ለተጠናወተህ “የታሪክ ምሁር” ተብዬው ዶ/ር ኃይሌ ላሬቦ፤ በኦሮሞዎች ተገደሉብኝ ላልከው ቤተሰቦችህ ታሪክን በመበቀያነት መጠቀምን አቁም!

Posted: Guraandhala/February 23, 2014 · Finfinne Tribune | Gadaa.com | Comments

ሚኒሊክን  ብትወቅሱ  ማንነታችሁን ትረሱ” በሚል  አርዕስት  ፅፈህ  የለጠፍከዉን  ሀተታ አይቸዋለው።  የግዕዝ  ፊደሎችን  መፃፍ ባልችልም ፤  ጫፍ  የወጣ  ወገንተኝነትህና  ጥላቻህ  ፊደል  እየለቀምኩም ቢሆን  መልስ  እንድሰጥ  አስገድዶኛል። ለነገሩ  ቃለ ምልልህን  ከሰማሁ  ጊዜ  ጀምሮ  በኦሮሞ  ህዝብ ላይ  ልዩ ጥላቻ  እንዳለህ  የተረዳሁ  ቢሆንም  ምክንያቱ ምን  እንደሆነ ላውቅ  የቻልኩት  ከዚህ ፅሁፍህ ላይ  ነው፡፡  በዚህ ፁሑፊ ራስህን  ያልቻልክ  የስርአቱ ሰለባ  መሆንን ስላስመሰከርክ ፥  ይህ  መልስ ለስርአቱ  አቀነንቃኞች የተሰጠ ነው። ለማንኛውም  እስኪ  የፅሁፍህን  ይዘት ወደ  መገምገም  ልመለስ፡፡
የኢትዮጵያ ታሪክ
የኢትዮጵያ  ታሪክ  የዉሸት  ታሪክ  ነዉ።  ባለሟሎቹ  ነገስታቱን ለማስደሰት  ንጉሱን  በማሞገስ  ታረክ በማስመሰል ይጽፉለታል።  እንድያው ም  የኢትዮጽያ  ታረክ  ክብረ  መንግስት  ይባል  የለም:: ጠላቱን ደግሞ  በማዉገዝ  ያስደስቱታል።  እንግዲህ  እነ ደብተራ ዘነብ  እና  አባ  ባህሪ  ከዚሁ  ቡድን የሚመደቡ ናቸው፡፡  በተለይም  አባ  ባህሪ  ብእራቸውን  ከወረቀት  ጋር  ሲያገናኙ  የነገዱን ቁጥር  ብዛት ፣ ሰውን ለመግደል ያለዉን ትጋት ወዘተ እያሉ በጥላቻ  እና በጠላትነት  መንፈስ  ልክ  እንዳንተ  የፃፉ  በመሆናቸው  እነዚህን ታሪኮች  እንደ እውነተኛ  ታሪክ  አድርገህ  ልትከራከርባቸው  መሞከርህ  የታሪክ ምሁርነትህ ን  አጠያያቂ  ያደርገዋል፡፡  ይህ ማለት ልክ ዛሬ  የመለስ ደጋፊዎች  “የተለየ  ራዕይ ያለው፣  መልካም  መሪ”፣  በሚሊዮን  ዓመት  አንዴ  የተፈጠረ፣”  ወዘተ… እያሉ እየፃፉለት  ያሉት ነገ  ታሪክ  መሆኑ  አይቀርምና  ያኔ  እነዚህ  አጨብጫቢዎች  የፃፉለትን  እንደማጣቀስ  ይቆጠራል፡፡ ከኢትዮጵያ  ታሪክ ውስጥ ልናምናቸው  የምንችላቸው  እውነታዎች  ጥቂቶች  በመሆናቸው  ስለተፃ ፉ  ብቻ  አንቀበላቸሁም፡፡ በተቻለ  መጠን  ወገንተኛ  ባልሆኑ  አካላት  የተፃፉትን  መርጠን  እንጠቀማለን፡፡
የግል ጥላቻ
ከከንባታ ጎሳ  የተወለድክ  መሆንህን  ጠቅሰህ  የአርሲ  ኦሮሞዎች  እናትህን፣  የእናትህን  እናት(አያት) እና  በአጎትህ ላይ  ጭፍጨፋ  መፈፀማቸውን  ጠቅሰሀል:: ድርጊቱም  የተፈፀመው  በጎሳ  ግጭት ሳቢያ  መሆኑን  ገልፀሀል፡፡ ለመሆኑ የከንባታ  ጎሳ  በጦርነት  የበላይነትን  ቢያገኝ  አርሲዎችን  አይገልም ነበርን? የአበባ  ጉንጉን  ነበር  ወይ የሚያጠልቁላቸው? እንዲህ  አይነት ጦርነቶች  በጎሳዎች መካከል  የተለመዱ  ስለሆኑ  የኦሮሞን ጨካኝነት ለማሳየት ይህንን  በምሳሌነት መጥቀሽ  ያንተን  ወገንተኝነት  እና  የበቀል  ስሜት  ከማሳየት ውጪ  ምንም  እርባና  የለውም፡፡
አኖሌ
የአኖሌ  ታሪክ  እንደሚያስረዳው  በአኖሌ  የተፈፀመው  የቀኝ  እጅ  እና ጡት  ቆረጣ  በጦርነት  ወቅት  የተፈፀመ  አልነበረም:: ይህ  ድርጊት  የተፈጸመው  በራስ  ዳርጌ  በተመራው  ስድስት  ዙር  ዘመቻ  አራቱን  አርሲዎች  ያሸነፉ  ቢሆንም በመጨረሻ  “አዙሌ” በተባለው  ቦታ  በተደረገው ጦርነት  በቁጥር  120,000 (አንድ  መቶ  ሃያ  ሺህ) የአርሲ  ጦረኞች ከተገደሉ  በኋላ  የነፍጠኛው ጦር  አሸንፎ  አርሲን  ሊቆጣጠረው  ችሏል፡፡  ከዚህም  በኋላ  ቢሆን  የአርሲ ኦሮሞዎች በተፈለገው  መጠን  አልገብር  ስላሉ  እና  በተበታተነ  ሁኔታ ማጥቃት  ባለማቆማቸው  አኖሌ  በተባለው  ቦታ  “ሰላም እናወርዳለን  እና  የእርቅ  ጉባኤ  ተሳተፉ”በማለት  ነፍጠኞቹ ነጭ  ባንዲራ እያውለበለቡ  ህዝቡ  እንዲሰበሰብ  ካደረጉ በኋላ  በሦስት  ሺህ  አርሲዎች  ላይ  አሰቃቂውን  የቀኝ  እጅ  እና  የጡት ቆረጣ  ፈፀሙ፡፡ (ይህን  በተመለከተ  የዶክተር አባስ  ሀጂን  መፀሀፍ  አንብብ) ይህ  የቀኝ  እጅ  ቆረጣ  በአድዋ  ጦርነት በተማረኩት  የኤርትራ አስካሪዎች  ላይም ተፈፅሟል።  ስምንት መቶ ወታደሮች ቀኝ  እጅ  እና  እግራቸውን  በአፄ  ሚኒሊክ ትዕዛዝ  ተቆርጧል፡፡ ይህን ሲያደርጉ ግን  ከነዚህ  ጋር የተማረኩትን  የጣሊያን ወታደሮች ምንም  ሳያደርጉ  ነበር  የሸኟቸው፡፡  ይህም  አፄዉ የፈረንጅ  አጎብዳጅ  መሆናቸውን  ያሳያል፡፡  ይህ  በኤርትራ  አስካሪዎች  ላይ የተፈፀመው  ድርጊት  እንደዚህ  አይነት የጭካኔ  እርምጃ  የተለመደ መሆኑን  ማሳያ ነው፡፡  በተጨማሪም  “አፄ  ሚኒሊክ  እጅግ ተዋረዱ የሸዋን  ነገስታት  እጅ ነስተው  ሄዱ” የሚለው  ቅኔ  እጅ  የመቁረጥ  ባህል ስር  የሰደደ  መሆኑን  ማሳያ  ነው።  ጳዎሎስ  ኞኞ  አፄ ቴዎድሮስ አንድ ጊዜ  አራት  መቶ  ሰው  ሌላ  ጊዜ  ስድስት  መቶ  ሰው  እጅ  ቆርጠው አንገታቸው  ላይ  አንጠልጥለው  እንዲሄዱ  ያደረጉ መሆኑን  እና  ይህም  በተለያየ  ጊዜ  ይፈፀም  እንደነበር  ፅፏል፡፡
ጨካኝነት
ኦሮሞ  በጦርነት  ሲያሸነፍ  “ጨካኝ” ይሉታል።  ሲያሸነፋቸዉ  “ፈጀው፣ ጨፈጨፈው፣ ጨረሰው” በማለት  እና አቢሲኒያውያን  የኦሮሞን ህዝብ  ሲያሸንፉ  ደሞ  “ዛሬ  አምላክ  አሳልፎ በእጃችን  ሰጠ” አንገታቸውን  ቆራርጠን ጭንቅላታቸውን  ከመርን።  በእግዚአብኤር  ኃይል  ይህን  ያህል  ገደልን      እያለ  ኦሮሞን  መግደል  ፅድቅ  እንደሆነ  አድርጎ ይጽፍ  የነበረው  አባ  ባህሪ  ነበር።  በውጊያ  እነሱ ሲያሸንፉ  ጀግንነት  እና  የአምላክ  እርዳታ፤  ኦሮሞ  ሲያሸንፋቸው ደሞ  እንደ  ጨካኝነት መቁጠራቸው ወገንተኝነትን  እና  ጥላቻን  ከማንፀባረቅ  ውጪ  ሌላ ምንም  ፍቺ  የለውም።  ጦርነት ከሆነ  ጦርነት ነው:: ኦሮሞ  እየተወጋ  ዝም  አይልም።  ምናልባትም  ወግተውት  አፀፋውን  ሲመልስ  መንጫጫቱ  “አንቺው ታመጪው  አንቺው  ታሮጪው” መሆኑ ነው፡፡  በሌላ  የሕግ  መርህ  ባለቤት  በራሱ  ጉዳይ  ፈራጅ  አይሆንም  ስለሚባል በራሳችሁ  ጉዳይ ለራሳችሁ  የሰጣችሁት  ምስክርነት ተአማንነት  አይኖረውም፡፡  እንዲሁም  ጠላት  ነው  ብላችሁ በጥላቻ እና  በፍራቻ  ስለምታዩት  የኦሮሞ  ህዝብ  የምትሰጡት  ምስክርነትም  ቢሆን  ከወገንተኝነት  የፀዳ  ሊሆን  አይችልም።  ይህ ሁሉ  ሆኖ ግን ኦሮሞን  ከሚጠሉት  ጎራ  ካሉት  ፀሀፊዎች  እንደ  እነ  አለቃ  ታዬ  አይነቶቹ  በመፀሀፋቸው  ኦሮሞ  ሰላም ወዳድ፣ እግዚአብሄርን  የሚፈራ፣  በሸንጎው  በውሸት  የማይፈርድ፣ ምንም እንኩዋን  ክርስትናን  ያልተቀበለ  ቢሆንም አስርቱን  ትዕዛዛት  “ክርስቲያን  ነን” ከሚሉት  በላይ  ያከብራል  በማለት መስክሯል። ምንም  እንኩዋን  ክርስቲያኖች ብንሆንም  ክፉዎች  እና  በመፀሀፉ  የማንመራው  እኛ ነን  እንጅ  “ኦሮሞ እንኩዋን  በሰው  በእንስሳ  እንኩዋን  አይጨክንም” በማለት  በሰፊው  ያተተውን  እንድታነብ  እጋብዝሀለው፡፡ ይህንን  የዋህ  እና  ሰላም  ፈላጊ  ህዝብ  ጫና እና  ጥቃት  ካበዛችሁበት  በኋላ  እሱ  አምርሮ  አፀፋውን ሲመልስ  “ጨካኝ” እያላችሁ  ብትንጫጩ  ማንም  አይሰማችሁም። ኦሮሞ  ጀግና  እንጂ ጨካኝ  አይደለም፡፡  ስለ  ኦሮሞ  ጀግንነት  በደንብ  አድርጋችሁ ታዉቃላችሁ።  በአድዋ  ጦርነት የአምባላጌን ምሽግ  የሰበረዉ  በማን  የተመራ ጦር  ነዉ? ገበየሁ  ገቦ  አይደለም  እንደ?  ሚኒሊክ  ፈርቶ ስደራደር ፣ ገበየሁ  ሳይታዘዝ  ድል  አድርጎ  በዉጊያዉ ተገደለ::  ፈረንጆቹን  ፈርቶ መቐለ ላይ የሸኛቸዉ ሚኒሊክ፣  ጣይቱ  ባትኖር ከጣሊያን  ጋ  ይዋጋ  ነበር? ኢትዮጵያዊነትን  እንድንቀበል ለማባበልም ብሆንም  ጣይቱ  ኦሮሞ  መሆኗን  አምናችኋል::
ወራሪ
የኦሮሞ  ህዝብ  የኩሽ  ዝርያ ነው፡፡  ይህ  የኩሽ ነገድ  ህዝብ  ከደቡባዊ  ግብፅ  ጀምሮ  በዛሬይቷ  ሱዳን  እና  በአፍሪካ ቀንድ ለብዙ  ሺህ ዓመታት  በመኖሩ  ይህ  አካባቢ ለኩሾች ጥንት  መኖሪያቸው  ነው፡፡  ከደቡብ  የመን  ከ700 ዓመተ አለም  እስከ  100 ዓ.ም  ፈልሰው ወደ  አፍሪካ  ቀንድ  የመጡት  ሀበሻ እና  ሀማሴን  የተባሉት  የሴም  ዘሮች  ናቸው፡፡ የኩሽ  ነገድ የሆኑት  እነ  ሲዳማ፣  ሀዲያ፣  አፋር፣  ሱማሌ፣  አገው፣  ሁሉ አገራቸው  የአፍሪካ  ቀንድ  መሆኑ  እየታወቀ የኩሽ  ነገድ  የሆነው ኦሮሞን  ብቻ  የህንድ  ውቂያኖስን  አሻግራችሁ  ስታሰፍሩት  እፍረት  ነገር  አልፈጠረባችሁም፡፡ “የአብዬን  እከክ  ወደ  እምዬ ልከክ” እንደሚባለው  መጤ  የሆነው  የሴሜቲክ  ነገድ  ነባሩን  ህዝብ  ወራሪ  የማለት የሞራል  ብቃት  የለውም፡፡  አባ ባህሪ  ኦሮሞዎች  ገላና  የተባለውን ወንዝ ወደ ምስራቅ  አቋርጠው መጡ  ይበል  እንጂ  ይህ ገሞ የተባለው  ቦታ ጋሞ  ጎፋ ስለመሆኑ  ምንም ደጋፊ ማስረጃ  የለም፡፡  እዚህ ላይ  ሁለት ግልጽ  ያልሆኑ ጉዳዮች  አሉ፡፡  በመጀመሪያ፣  ገላና የትኛው ወንዝ  ነው  የሚል  ጥያቄ  ያስነሳል፡፡  ገላና  ማለት ወንዝ  ወይም ትልቅ ውሃ  ከማለት ውጪ  ገላና  የሚባል ወንዝ  የለም፡፡  የሰገን  ወንዝ  ወይም  ገላና  አባያን  አቋርጠው  ወደ  ጋሞ ጎፋ  መጡ  እንዳይባል  ወደ ምስራቅ  እንጂ ወደ ምእራብ  ተሻገሩ  አላሉም፡፡  አባያ  ከጋሞ  ጎፋ  በምእራብ  በኩል  ስለምትገኝ  አባያን  ከተሻገሩ  ወደ  ምእራብ ተሻገሩ  ማለት ነበረበት፡፡  ሌላኛው  አወዛጋቢ ጉዳይ  አባ  ባህሪ  ገሞ  ከማለት  ውጪ  ከገሞ  እስከ  ሸዋ  መካከል  ባለው ሰፊ  አካባቢ ምንም  ገጠመኞች ሳይፅፉ  በግንደበረት፣  በጎጃም  እና  በሌሎች  ሸዋ  አካባቢዎች  የተደረጉ  ጦርነቶች  እና ግጭቶችን  ብቻ  ማተታቸው  እንዲሁም  በሰሜን  ሸዋ  አካባቢ እና  በሌሎች  ሸዋ  አካባቢዎች  ገሞ ተብለው  የሚጠሩ ቦታዎች መኖራቸው  አባ  ባህሪ  የነበሩት  በሰሜን  ሸዋ  አካባቢ እንጂ  ጋሞ  ጎፋ  አልነበረም  የሚል  ድምዳሜ  ላይ  ያደርሳል፡፡ በተጨማሪም  አባ  ባህሪ  ከነበሩበት ገሞ  ከሚባለው  ቦታ  ሸሽተው  ወደ ደብረ  ዳሞ  ነው  የገቡት፡፡  በደብረዳሞ  እና በገሞ  መካከል  ያለው  ርቀት  አጭር  መሆኑን  ከፅሁፋቸው  ማወቅ  ስለሚቻል  የነበሩበት ቦታ  ሸዋ  ውስጥ  መሆኑን  የበለጠ የሚያረጋግጥ  ነው፡፡
የዘር ግንድ
በዚህ  ፅሁፍህ  የኦሮሞ ህዝብ  ነገድ  እንጂ  የዘር  ግንዱ  አይተሳሰርም፡፡ ከአንድ  የዘር  ግንድ  የወጣ  አደለም፤ በቋንቋም  በባህልም  አይገናኝም  ብለሃል፡፡ ይህ  ትልቅ  ስህተት ነው፡፡ ለፅሁፍህ  ዋቢ  ያደረከው  በዋናነት  የአባ ባህሪን  መፀሀፍ  ሲሆን፤ አባ  ባህሪ  ደግሞ  ኦሮሞ  ከአንድ  የዘር  ግንድ  የተገኘ  አንድ  ህዝብ  መሆኑን  አልካደም፡፡ እንደውም ኦሮሞ  ቦረና  እና  ባሬንቱማ  በሚባሉ  ሁለት ትላልቅ  ጎሳዎች ስር  የተደራጀ  መሆኑን  ጠቅሶ  የቦረና  እና የባሬንቱማ ልጆች  እነማን  እንደሆኑ  በመዘርዘር  ህዝባቸው  በመብዛቱና አገራቸው  በመራራቁ  በተለያዩ ገዳዎች  ስር መተዳደር  መጀመራቸውን  አትቷል፡፡  በዚህም  መሰረት  የቦረና  ኦሮሞዎች ኦዳ  ነቤን ማእከላቸው  ሲያደርጉ  ባሬንቱማዎች ደግሞ ማእከላቸውን ኦዳ  በቡልቱም  አድርገዋል፡፡  ያለምንም  እፍረት  የኦሮሞ  ህዝብ  በቋንቋም  በባህልም  አይገናኝም በማለትህ  እኛ  አፍረንልሀል፡፡  ይህ  ህዝብ  የአንድ  ቋንቋ  ባለቤት፤  በገዳ ስርአት  ሲተዳደር  የነበረ  እና  አንድ ሃይማኖት  “ዋቄፈና”  የነበረው  ህዝብ  ነው፡፡  አንተም  ሆንክ  አባ  ባህሪ፣  የኦሮሞ  ህዝብ ዘሩን  ቆጥሮ  ከአስራ  አምስት እስከ  ሃያ  አባት  ድረስ  የትኛው  ጎሳ  ከየትኛው ቅርንጫፍ  እንደሆነ  እንደሚያውቅ  ታውቃላችሁ፡፡  “ጋላ” የሚለው  ቃል ኦሮሞን  አይወክልም  ብለህ  ያቀረብከው ኦሮሞን ለመከፋፈል  ካለህ  ፍላጎት  እንጂ  ከኦሮሞ  በስተቀር  በዚህ  ስም  ሲሰደብ ወይም  ሲጠራ  የነበረ  ሌላ  ብሄርም  ሆነ  ብሄረሰብ  የለም፡፡  አለመኖሩን በደንብ እያወክ  ይሄን  ህዝብ ለመከፋፈል ባለህ  እኩይ  አስተሳሰብ ህዝቡ  በቋንቋም  በባህልም  ሆነ  በዝርያ  በጭራሽ  አይገናኝም ማለትህ  በእጅጉ  የሚያሳፍር ነው፡፡
የገዳ ስርአት
የገዳ  ስርዓት  ስልጣን  ከአንድ  ቡድን  ወደ  ሌላ  ቡድን  በሰላማዊ መንገድ  የሚተላለፍበት  ስርዓት ነው፡፡  ይህ  ስርዓት በየስምንት ዓመት  እድሜ  እርከን  የስራ  ድርሻ  በመከፋፈል  ህብረተሰቡን በአምስት  የፖለቲካ  ፓርቲዎች ስር በማደራጀት  አምስቱ  ቡድኖች  ተራ  በተራ ለስምንት  ዓመት  የሚያስተዳድሩበት  ስርዓት ነው፡፡  “በዚህ  ሹመት  ላይ ባለ  ግዜ  ውስጥ  ሰው  ካልገደለ  ጠጉሩን  አይላጭም  ጉቱን  አያሳድግም” ብለሃል፡፡  ይህ  ከእውነት  የራቀ  እና  ከጥላቻ የመነጨ  አገላለፅ  ነው፡፡  አንድ  ጉዳይ ግን  አለ፡፡  ሁሉም  ሉባ  የራሱ  የሆነ  የሚያከናውነው ተልዕኮ  አለው፡፡ ለምሳሌ  በጠላት  የተያዘ  መሬት  ካለ  የማስለቀቅ ግዴታ  ስለሚኖርበት ያንን  ጉዳይ  እስካላከናወነ  ድረስ  እረፍት አይኖረውም፡፡
ገዳ  የኦሮሞ  መንግስ  ስለሆነ ልክ  ቡሽ  የጀመረውን  ጦርነት ኦባማ  እንደሚጨርሰው  ሁሉ  የሙደና  ገዳ  የጀመረውን የሮበሌ  ገዳ  ይጨርሰዋል፡፡  ይህን  ከአደራ  ጋር  የተሰጠውን ተልህኮ  ሳያሳካ  እረፍት  አይኖረውም፡፡  ይህ ዳር ድንበሩን  መከላከል  እና  የብሄሩን  ክብር  ማስጠበቅ  እነ  አባ  ባህሪ  በስርዐቱ  ጥንካሬ  ምክንያት  በደረሰባቸው ሽንፈትየተነሳ  የቻሉት  ያህል  ስርዐቱን  አሉታዊ  አስመስለው  ስለፃፉ  የስርዐቱ ዲሞክራሲያዊነት  አያሳጣውም፡፡  የገዳ ስርዐት  የኦሮሞን  ህዝብ  በእኩልነት  እና  በዲሞክራሲ  እንዲኖር  ያስቻለና በተሻለ  አደረጃጀት  የኦሮሞ  ህዝብ በጎረቤቶቹ  ላይ  በጦርነት  የበላይነትን  ያጎናፀፈው  በመሆኑ  የኦሮሞን  ህዝብ  የሚጠሉ  “አባ  ባህሪዎች” እና ተሸናፊዎች  ይህንን  ስርዐት  ሊወዱት  አይችሉም፡፡
ሰለባ
መስለብ  የሰሜቲኮችና  የአማራ  ባህል  ነዉ።  ማስርጃ  ፩።  በመጽሀፍ ቅዱስ  መጽሀፈ ነገስት ዉስጥ  ዳዊት  የሳኦልን  ልጅ ለማግባት  የፊልስጤማዉያን  ብልት  ቆርጦ ማምጣቱ፥፥  ዳዊት  የሰለሞን  ኣባት ነዉ።  የሰለሞን  ልጆች ነን  የሚሉት እነማን  እንደሆኑ  ማስረዳት  አይጠበቅብንም። ማስርጃ  ፪።  በመጽሀፍ ቅዱስ  የሀዋርያት  ሥራ  መጽሀፍ  አንድ ኢትዮጵያዊ  ጃንደረባ  ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዞ  ነበር።  ይህ ግዜ  በግምት ፩ኛ  ክፍለ  ዘመን  ነዉ።  ሰዉየዉ ከሰሜን  ኢትዮጵያ  ስለመሆኑም  ግልጽ  ነዉ።  ማስርጃ  ፫  ። ኮሎኔል  አልኸንድሮ  ዴል  ባየ  የተባለው  የኢትዮጵያ ወዳጅ በጻፈዉ  “ቀይ  አንበሣ”  በተሰኘዉ  መጽሀፍ ውስጥ አማሮች  ከ፲  እስከ ዕድሜ  የሆኑ  ህጻናትን  ብልት  እየሰለቡ የንጉሶች፣ የራሶች  እና  የፊታዉራሪዎች  አገልጋይ ጃንደረባ  ያደርጏቸዉ  እንደነበር  ጽፏል።  ድምጻቸዉ ወደ ቀጭንነትም ስለምቀየር  ቤቴ  ክርስቲያን  ዉስጥም  ይቀድሱ  እንደነበር  ይታወቃል።
ስልጣኔ
ሌላው  በፅሁፍ ውስጥ  ልትገልፀው  የሞከርከው  የኦሮሞ ህዝብ  ኃላቀር  እንደሆነ ልታሳይ  የሞከርከው  ሙከራ ነው፡፡ በዚህ  ሙከራ  ዘላንነትን  (አርብቶ አደርነት) የአኗኗር  ዘይቤ መሆኑን ረስተህ  እንደ  ኃላቀርነት ለማየት  መሞከርህ ምን  ያህል  ኃላቀር  እንደሆንክ  የሚያሳብቅ ነው፡፡  ክርስቲያን  አለመሆን ወይም  በአፍሪካዊ  እምነት  (ዋቄፈና) ተከታይ  መሆንም  ቢሆን  ሊደነቅ  እና  ሊኮራበት  የሚገባ  እንጂ  እንደ  ኃላቀርነት  ሊታይ  አይችልም፡፡  የራስ  የሆነ የእምነት ፍልስፍና  የዛን ህዝብ  ታላቅነት  የሚያሳይ ነው፡፡
አፄ ሚኒሊክ
1. ቡላቶቪች  የተባለው ራሺያዊ  በ1900 ከሚኒሊክ  ጦር  ጋር  ዘምቶ  የነበረ  ሲሆን  “Ethiopia though Russian Eyes” በተሰኘው  መጸሀፉ  የሚኒሊክ  ወረራ  የኦሮሞን ህዝብ  ቁጥር  በግማሽ  ያሳነሰ  መሆኑን  ጠቅሷል፡፡
2. ማርቲን  ዴሳልቫክ  የተባለ  ፈረንሳዊ  የካቶሊክ ሚሺነሪ  (1900) “The Oromo: An Ancient Africa Nation” በተባለው  መጸሀፋቸው  በዚህ  ወረራ  የኦሮሞ ህዝብ  ቁጥር  በግምት  ከአስር  ሚሊየን ወደ  አምስት ሚሊየን  መውረዱን  ገምቷል፡፡
3. August 18, 1895 እ.አ.አ  የታተመው  የኒውዮርክ  ታይምስ  ጋዜጣ  አፄ  ሚኒሊክ  በኦሮሞ ላይ  ዘመቻ በመክፈት  ወንዶቹን  በመፍጀት ሕፃናት  እና ሴቶችን  በባሪያነት  መውሰድ  በሰፊው  ይተገበሩ  እንደነበር  ፅፏል፡፡
4. February 26, 1895 እ.አ.አ  የታተመው  የኒውዮርክ  ታይምስ  ጋዜጣ  አሰቃቂው  የሚኒሊክ ዘመቻ  በሚል ርዕስ  ስር  ሰሞኑን  ንጉስ  ሚኒሊክ  በኦሮሞ ህዝብ  ላይ  በደቡብ  አቢሲኒያ  የከፈቱት  ዘመቻ  70,000 ሰዎችን በመግደል  15,000 መማረካቸውን  ገልፀዋል፡፡
5. August 2,1874 እ.አ.አ  የታተመው  የኒውወርክ  ታይምስ ጋዜጣ  የአቢሲንያ  ባሪያዎች  በሚል  አርስት  ስር በየዓመቱ  ከ80,000 እስከ  90,000 የሚሆኑ  ባሪያዎች  በምፅዋ  ወደብ  በኩል ወደ ውጪ  የሚሽጡ  መሆኑን  ጠቅሶ የባሪያ  ነጋዴዎቹ  ባሪያዎችን  የሚገዙት  ከነፍጠኞቹ  ሲሆን  ንጉሰ ነገስቱም  የቀረጡ  ተቋዳሽ  መሆኑን  ያትታል፡፡
6. አኖሌ  ላይ  የሦስት ሺህ ኦሮሞዎች  እጅ  እና  ጡት  ከማስቆረጣቸው  በተጨማሪ  በአደዋ  ጦርነት  የተማረኩ  800 የኤርትራ  አስካሪዎችን  ቀኝ  እጅ  እና  ቀኝ  እግር አስቆርጠዋል፡፡
7. November 7, 1909 እ.አ.አ  የታተመው  የኒውዮርክ  ታይምስ  ጋዜጣ  በአርስቱ  የአቢሲኒያው  ንጉስ  ሚኒሊክ በአሜሪካው  የባቡር  ሃዲድ  ስራ ተቋራጭ  ከፍተኛ  የአክሲዮን  ባለቤት ናቸው  በማለት  ወደ  ዝርዝሩ ውስጥ  ስንገባ  ይህ የባቡር  ሃዲድ  አክሲዮን  ከሃያ  አምስት  ሚሊዮን ዶላር  በላይ  መሆኑ  እና  ከዚህ  በተጨማሪ  በቤልጅየም  እና እስካንዲኒቭያ  ከተሞች  የወርቅ  አምራች  ኩባንያ ውስጥ  አክሲዮን  እንዳላቸው ዘርዝረዋል፡፡  ይህ ሁሉ  ንብረት  ከዬት መጣ  ብለን  ብንጠይቅ  ከተወረሩ  ብሄር  ብሄረሰቦች  የተዘረፈ መሆኑ  ግልፅ  ነው፡፡  በዚሁ  መሰረት  የሚኒሊክ  ወታደሮች ከአርሲ  66,000 የቀንድ  ከብት  (ፕሮፌሰር  መኩሪያ  ቡልቻ)፤  ከወላይታ  18,000 (ተሻለ) ከደቡብ ኦሞ 40,000 ከጂጂጋ  50,000 (ጆን  ማርካኪስ) ወዘተ… የተዘረፈ  ነው፡፡ ከ፩ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጽያዊያኖችን በባርነት ሸጠዋል(መኩሪያ  ቡልቻ)::
8. አፄ  ሚኒሊክ  ከምእራብ  ኢንዲያ  ወደ  አዲስ  አበባ  መጥቶ  የጥቁር  ህዝብ  መሪ  ሁንልን  ብሎ  የጠየቀውን  ቤኒቶ ሲልቪያን  የተባለውን  ሰውዬ  እኔ  ጥቁር  አይደለሁም፡፡  ሴማዊ  ነኝ  በማለት  አባረውታል፡፡  ሀይለስላሴም  HO Davis የተባለው  ታዋቂው  የጥቁር  መብት  ታጋይ  እና  Marques Garvey የተባለው  ጃማይካዊ  የጥቁር  መብት  ታጋይ ባናገሩት  ጊዜ  እኔ  የሰለሞን  ዘር ነኝ  በማለት  አፍሪካዊነታቸውን  ክደዋል፡፡  እነዚህ  በአፍሪካዊነታቸው  የማያምኑ፣ በአፍሪካዊነታቸው  የሚያፍሩ  የበታቸው  ስነ ልቦታ  የተጠናወታቸው  እና በራሳቸው  የማይተማመኑ  ናቸው፡፡
9. ተወራሪው  የደቡብ  ህዝብ  መሬቱን ተነጠቀ፤  ነፍጠኞቹ  መሬቱን ተከፋፍለሁ ለሚፈልጉት  ሰጡ፡፡  በሃብት ንብረቱ ላይ  አዘዙበት  ህዝቡ  ወደ  ባርነት ወረደ  :: መሬት  አልባ፣  ታሪክ  አልባ፣  ባህል  አልባ፣  ሀይማኖት  አልባ፣  አረመኔ ህዝብ  ብለው  ሰደቡት፡፡
ያልተሳካዉ  ፕሮጀክት
እናንተማ  እጃቸውንና  ጡታቸውን  ቆርጠን  አዋርደናቸዋል፤በማንነታቸዉ እንዲያፍሩ  አድርገናቸዋል፤ ስነልቦናቸውን ሰልበናል፤  ቋንቋውን  እና  ባህሉን ቀብረናል  ብላችሁ  ተዝናንታችሁ ነበር:: “የዋሆች  ምድርን  ይወርሳሉ” የተባለው ቃል ይፈፀም  ዘንዳ ግድ  ነውና  ከአንድ መቶ  ሰላሳ  ዓመታት  በኋላም  ስነ፡ልቦናው፣  ቋንቋው፣  ማንነቱ፣  ባህሉም ተጎዳ  እንጂ አልጠፋም:: ምንም  እንኩዋን  የወሎ ኦሮሞ  ጎሳዎች  የነበሩት  እነ  የጁ፣ ወረ  ቃሉ፣  ወረ  ሂመኖ፣  ወረ  ባቦ፣  ወሎ፣ ወረ  ሼህ፣  ለገ  አምቦ፣  ራያ፣  እና  አዜቦ  የመሳሰሉትን  ማንነታቸውን  እና ቋንቋቸውን  በማስቀየር  ቢሳካላችሁም ከዘጠና  በመቶ በላይ  የኦሮሞ  ህዝብ  ማንነቱ  ያልተፋቀ  በመሆኑ ፕሮጀክታችሁ  ባለመሳካቱ ኢትዮጵያዊ  ማንነት  እንጂ ሌላ  ማንነት  የለም  እያለችሁ  ብታለቃቅሱ  አይፈረድባችሁም::
ማጠቃለያ
አሁን  የሚታለቅሱት  የተወራሪ  ብሄርና  ብሄርሰቦች  ቋንቋ፣ ባህል፣  ሀይማኖትና  ማንነት ለማጥፋት  አያቶቻችሁ  የነደፉት ፕሮጀክት  ባለመሳካቱና  የከተሞቹን  ስም ለውጣችሁ፣  የሰዎችን  ስም  አስቀይራችሁ፤ ቀብረነዋል  ብላችሁ  ያሰባችሁት  ህዝብ  የወጠናችሁት ሁሉ ሳይሳካ ቀርተዋል።  የጭቁን  ህዝብ ትግል  እያሸነፈ ሲመጣ የሚትጮሁ  የፊውዳል  ቡችሎች  ሆይ እናንተ  ትቀበራላችሁ  እንጂ  የሰፊው  ህዝብ  ቋንቋ፣  ሀይማኖት፣  ባሀል  ይለመልማል  እንጂ ወደ  ኋላ  ስለማይመለስ  እርማችሁን  አውጡ፡፡  አረመኔ፣  ኋላ  ቀር፣  ያልተገረዘ፣  ወራሪ፣  ታሪክ አልባ፣  አገር  አልባ፣  ዘላን  ብላችሁ  ብትሳደቡ  የህዝቡን  ቁጣ  ከመቀስቀስ  እና  የህዝቦችን  ተቻችሎ  አብሮ  መኖር እና  ሠላምን  ከማደፍረስ ውጪ  የማንነት  ስነ-ልቦና ልትጎዱ  ስለማትችሉ  በ130 ዓመት ውስጥ  ያልተሳካው  አሁን ሊሳካላቹ  አይችልምና  ለሞት  የተቃረበ ሰው  ከሚናዘዘው ኑዛዜ  ለይተን አናየውም፡፡

Saturday 22 February 2014

“አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ ተሳፋሪው የተደነቀው በረዳት አብራሪው ችሎታ ነበር” – በተጠለፈው አውሮፕላን ውስጥ የነበረው ኢትዮጵያዊ ይናገራል

ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ስዊዘርላንድ ላይ ተጠልፎ ባረፈው አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍሮ የነበረውን ኢትዮጵያዊ ቃለምልልስ አስነብቧል። ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ እንዲሰጥ በሚል እንደወረደ አቅርበነዋል።

“የተሳፋሪው ፍላጎት የሆነ መሬት ላይ ማረፍ ብቻ ነበር”


በሃዋሳ ከተማ በተለምዶ ኬሮ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተወልዶ ያደገው ወጣት ምህረቱ ገብሬ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በቀድሞው ሀዋሳ ኮምቦኒ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ነው የተከታተለው። የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና የመሰናዶ ትምህርቱንም በቅዱስ ዳንኤል ኮምቦኒ የሁለተኛ ደረጃና የመሰናዶ ት/ቤት አጠናቋል። ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2001 ዓ.ም በሲቪል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ካገኘ በኋላም፤ እስከ 2004 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመምህርነት አገልግሏል፡፡ በመቀጠልም ነጻ የትምህርት ዕድል በማግኘት፣ ወደ ጣሊያን አምርቶ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል፡፡
በቅርቡ ለእረፍት ወደ አገሩ የመጣውና በሃዋሳ ቆይቶ ወደ ጣሊያን ለመመለስ አውሮፕላን የተሳፈረው ምህረቱ፣ ባለፈው ሰኞ በረዳት አብራሪው ተጠልፎ ጄኔቭ እንዲያርፍ በተደረገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት 200 ገደማ ተሳፋሪዎች ውስጥ አንዱ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት በጣሊያን የሚገኘው ምህረቱ፣ የጠለፋውን አጋጣሚ በተመለከተ ጋዜጠኛ አንተነህ ይግዛው በኢ-ሜይል ለላከለት ጥያቄዎች የሰጠውን ምላሽ እንደሚከተለው አጠናቅረን አቅርበነዋል፡፡
የጉዞው አጀማመር ምን ይመስል ነበር?
አርፍዶ ወደ አውሮፕላን ጣቢያ መምጣት የሚያደርሰውን ጣጣ ስለማውቀው፣ አውሮፕላኑ ከሚነሳበት 50 ደቂቃ ያህል ቀድሜ ነበር የተገኘሁት፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ማለት ነው፡፡ ያው ጉዞው ሲጀመር እንደሌላው ጊዜ ሁሉ ስርአቱን የጠበቀና ሰላማዊ ነበር። አውሮፕላኑ ከበራራ ሰዓቱ ሰባት ደቂቃ ያህል ዘግይቶ ነበር የተነሳው።
አውሮፕላኑ ውስጥ አቀማመጥህ እንዴት ነበር? የት አካባቢ ነው የተቀመጥከው?
የመቀመጫዬ ቁጥር 27F ነበር። የተሳፈርንበት ቦይንግ 767 በርዝመቱ ትይዩ 7 የመቀመጫ መደዳዎች አሉት። ሁለት ሁለት መደዳዎች በሁለቱም ጥጎች እና ሶስት መደዳዎች መሃል ላይ። እኔ የተቀመጥኩት ከመሃል ሶስቱ መደዳዎች የመሃለኛዋ ወንበር ላይ ነበር። ከበስተግራዬ ያለችው ወንበር ላይ የተቀመጡት ሪካርዶ የተባሉ የ85 አመት የዕድሜ ባለጸጋ ጣሊያናዊ ነበሩ፡፡ በቀኜ በኩል እንዲሁ በግምት በስድሳዎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሌላ ጣሊያናዊ ተቀምጠው ነበር፡፡ ተዋውቀን ነበር፣ አሁን ግን ዘንግቼዋለሁ። ኢትዮጵያን ተዟዙረው እንደጎበኟት እያጫወቱኝ ነው ጉዞውን የጀመርነው፡፡
ጉዞውስ እንዴት ነበር?
እንደማስታውሰው ጉዞው ሲጀመር ሰላማዊ ነበር። ከፓይለቱ ጋርም ግንኙነት (ኮሙኒኬሽን) ነበረን፡፡ እኔ ድካም ስለተሰማኝ ወዲያው አሸለብኩ፡፡ በረራው ከተጀመረ በግምት ከ1 ሰዓት በኋላ የሱዳን አየር ክልል ውስጥ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ. . . መብራት ሲበራ ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ የምግብ ሰዓት መድረሱ ገብቶኛል። ወደ ፊት አሻግሬ ሳይ ሆስተሶቹ እያስተናገዱ ከእኔ ፊት 4ኛ ይሁን 5ኛ ረድፍ ደርሰዋል። ሁሉም ተዘገጃጅቶ እየተጠባበቀ ነበር። በዚህ መሃል የፕሌኑ ፍጥነት ሲጨምር ይታወቀኛል፡፡ ከፍታዉም ሲጨምር በጆሮዬ ላይ በሚሰማኝ ስሜት አስተዋልኩ። በተሳፋሪዎች ፊት ላይ የመረበሽ ስሜት ሲፈጠር አየሁ። እኛ ኢኮኖሚ ክላስ ስለነበርን ከፊት ምን እየተካሄደ እንደነበር አላየንም። በኋላ ስሰማ ከፊት የነበሩትም የቢዝነስ ክላስ ተሳፋሪዎች ምንም መረጃ አልነበራቸውም፡፡
ከዚያም በድምጽ ማጉያው የሆነ ድምጽ ተሰማ፡፡ የረዳት አብራሪው ድምጽ ነበር።
“ተሳፋሪዎች ከ 12 ደቂቃዎች በኋላ ሚላን እናርፋለን” አለ ረዳት አብራሪው፡፡ ጥቂት ቆይቶም፣ “ስለተፈጠሩ አንዳንድ መጉላላቶች ይቅርታ እንጠይቃለን” ሲል አከለ-በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋ። የረዳት አብራሪውን ንግግር ተከትሎ የተወሰኑ ተሳፋሪዎች ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ አንዳንዶችም ጮክ ብለው ሲያወሩ ይሰሙ ነበር፡፡ ከኔ በስተግራ በኩል ሶስት አራት መደዳዎችን አልፎ ከፊቴ ተቀምጦ የነበረ አንድ ወፍራም ሰው፣ በጣሊያንኛ ቆጣ ብሎ እየጮኸ ተናገረ – “መጀመሪያ ሚላን ሳይሆን ሮም ነው ማረፍ ያለብን ፣ ወደ ሮም ውሰዱን!” በማለት። ሌሎችም የሰውየውን ሃሳብ ደገፉ፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው ተሳፋሪ ወደ ሮም ነበር የሚጓዘው። ረዳት አብራሪው ሚላን ላይ እንደምናርፍ መናገሩ ብዙዎችን አበሳጭቶ ነበር፡፡
እውነቱን ለመናገር፣ እኔ ግን ሚላን እንደምናርፍ ስሰማ ደስ ብሎኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ ሚላን ወራጅ ነኝ፡፡ ረዳት አብራሪው የነገረን አስራ ሁለቱ ደቂቃዎች እየተገባደዱ መሆናቸው ሲገባኝ፣ ከአውሮፕላኑ ለመውረድ መዘገጃጀትና ጓዜን መሸካከፍ ሁሉ ጀመርኩ። ሆኖም አስራ ሁለቱ ደቂቃዎች አልፈውም አውሮፕላኑ አላረፈም፡፡ ካሁን አሁን ሚላን አውሮፕላን ማረፊያ ደረስን እያልን ስንጠባበቅ፣ ሌላ አስራ ሁለት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ አሁንም ሌላ አስራ ሁለት ደቂቃዎች—
ተሳፋሪው ሁሉ ግራ በመጋባት ሰዓቱን ደጋግሞ መመልከትና እርስ በርስ በጥርጣሬ መተያየት ጀመረ። ከአስራ ሁለት ደቂቃዎች በኋላ ሚላን ላይ ያርፋል የተባለው አውሮፕላን፣ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ በአየር ላይ ቆየ፡፡ የሚገርመው ያን ያህል ጊዜ አየር ላይ መቆየቱ ብቻ አይደለም፡፡ አበራረሩ የተለየ ነበር፡፡ አንዴ ፍጥነቱን ጨምሮ ይከንፋል፣ ከዚያ ደግሞ ፍጥነቱን ይቀንስና ተረጋግቶ ይበራል፡፡ እንደገና ይፈጥናል፣ እንደገና ይረጋጋል፡፡ ግራ ገብቶን እያለን፣ ከመቅጽበት አውሮፕላኑ ማረፊያው ላይ ደርሶ ማኮብኮብ ጀመረ፡፡ ያንን ያህል ግዙፍ አውሮፕላን፣ በዚያች ጠባብ ቦታ ላይ ያለችግር ማሳረፍ መቻሉ፣ የረዳት አብራሪውን ብቃት ያሳያል፡፡ ለማንኛውም አውሮፕላኑ በሰላም አረፈና እኛም እፎይ አልን፡፡

አውሮፕላኑ ካረፈ በኋላ የተሳፋሪዎች ስሜት ምን ይመስል ነበር?
የሚገርመው ነገር፣ አውሮፕላኑ እንዳረፈ በተሳፋሪው ፊት ላይ ከታየው ደስታና እፎይታ በተጨማሪ፣ ተሳፋሪው ለረዳት አብራሪው የሰጠው አድናቆት ነበር፡፡ አብዛኛው ተሳፋሪ ስለረዳት አብራሪው ችሎታ ነበር ተደንቆ የሚያወራው፡፡ በከፍተኛ የአድናቆት ስሜት ተውጠው፣ ለረዳት አብራሪው ያላቸውን አድናቆት በጭብጨባና በፉጨት የገለፁም ነበሩ፡፡ እኔም በደመነፍስ ሳጨበጭብ ነበር፡፡ ሚላን ምድር ላይ በሰላም እንዲያሳርፈኝ ለፈጣሪዬ ያደረስኩትን ጸሎት የማውቀው እኔ ነኝ፡፡
ሚላን እንዳረፋችሁ ነበር የምታውቁት ማለት ነው?
የሚገርመው እኮ እሱ ነው!… አውሮፕላኑ መሬት ከነካ በኋላ ሁሉ፣ ተሳፋሪው በሙሉ ጣሊያን ሚላን እንዳረፈ ነበር የሚያውቀው፡፡ ሚላን እንደምናርፍ ነው ረዳት አብራሪው የነገረን፡፡ ትኬት ከፍለን የተሳፈርነውም ወደ ጣሊያን እንጂ ወደ ስዊዘርላንድ ለመሄድ አልነበረም። በዚህ ቅጽበት ጄኔቭ የምትባል ከተማ በምን ተአምር እንሄዳለን ብለን እናስብ?
ጄኔቭ መሆናችሁን ያወቃችሁት እንዴት ነው?
አውሮፕላኑ በሰላም ካረፈ በኋላ ተሳፋሪው ከጭንቀቱ ተገላግሎ መረጋጋት ጀመረ፡፡ አንዳንዶች ሞባይል ስልኮቻቸውን አውጥተው መነካካት ያዙ። በሞባይላቸው የኢንተርኔት መስመር በመጠቀም ጎግል ማፕ የተሰኘውን የአገራትና የከተሞች ካርታ የሚያሳይ ድረገጽ፣ ጂ ፒ ኤስ ከሚባለው አቅጣጫ ጠቋሚ ቴክኖሎጂ ጋር አያይዘው ሲመለከቱ፣ ፊታቸው ላይ ድንገተኛ መደናገር ሲፈጠር አየሁ፡፡ አንዱ ተሳፋሪ ሞባይሉ ላይ ያየውን መረጃ በመጠራጠር፣ የሌላኛውን ሞባይል ማየት ጀመረ፡፡ “የት ነው ያለነው?” ለሚለው ጥያቄ እርግጠኛ የሆነ መልስ የሚሰጥ ጠፋ፡፡ ግማሹ “ ኦስትሪያ ነን!” ሲል፣ ገሚሱ “የለም ፈረንሳይ ነን!” ብሎ ይመልሳል፡፡ አንዳንዱ “ጀርመን ውስጥ ነው የምንገኘው!” ይላል፡፡ ሌላው “ስዊዘርላንድ ጄኔቭ ነው ያረፍነው!” እያለ ይናገራል፡፡ ጭንቀትና ውጥረት የፈጠረው መደናገር ሊሆን እንደሚችል ያሰብኩት በኋላ ነው፡፡
ጄኔቭ ማረፋችሁንና አውሮፕላኑ መጠለፉን ያወቃችሁት እንዴት ነበር?
እያንዳንዱ ተሳፋሪ አውሮፕላኑ ያረፈበትን አገርና ከተማ በተመለከተ የየራሱን መላምት እየሰነዘረ ግራ ተጋብቶ ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ በዚህ መሃል ነው፣ ድንገት የአውሮፕላኑን ዋና አብራሪ ድምጽ የሰማነው። በረራው ከተጀመረ አንስቶ የዋና አብራሪውን ድምጽ ስንሰማ ለመጀመሪያ ጊዜያችን ነበር፡፡ ዋና አብራሪው በጣሊያንኛ ቋንቋ ነበር የሚያወሩት፡፡ በጣሊያን ቆይታዬ የቀሰምኳት ቋንቋ ብዙም የምታወላዳ አልነበረችምና፣ ደቂቃዎችን ከፈጀው የአብራሪው ንግግር የተወሰነችዋን ተረድቼ፣ ቀሪውን ከጎኔ ከተቀመጡት ጣሊያናውያን ጠይቄ ለመረዳት ሞከርኩ፡፡
አብራሪው ወደመጸዳጃ ቤት ሲወጡ ረዳት አብራሪው በር እንደዘጋባቸው፤ አውሮፕላኑን ለሰዓታት ሲያበር የቆየው ረዳት አብራሪው እንደነበር፤ አውሮፕላኑ ያረፈው ጄኔቭ መሆኑን፤ በተፈጠረው ነገር ማዘናቸውን መግለጻቸውን እንዲሁም እያንዳንዱ ተሳፋሪ የስዊዘርላንድ ፖሊሶች ለሚያደርጉት ምርመራ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ነገሩኝ፡፡ ተሳፋሪው ስለ ጠለፋው ያወቀው በዚህ ጊዜ ነው፡፡
ተጠልፋችሁ ያላሰባችሁት ቦታ እንዳረፋችሁ ስታውቁ ምን ተሰማችሁ?

እውነቱን ለመናገር በወቅቱ የሁሉም ተሳፋሪ ጸሎትና ምኞት በረራው በሰላም መጠናቀቁና አውሮፕላኑ አደጋ ሳያጋጥመው ማረፉ ብቻ ነበር፡፡ የተሳፋሪው ፍላጎት የትም ይሁን የት፣ ብቻ የሆነ መሬት ላይ ማረፍና ከጭንቀት መገላገል ነበር፡፡ አስበው እስኪ… ከአብራሪውም ሆነ ከሆስተሶቹ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት በሌለበት አደናጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ለሰዓታት የበረርነው፡፡ ከዚያ ደግሞ… ሮም የማረፍ ዕቅዱ ተሰርዞ፣ ከ12 ደቂቃዎች በኋላ ሚላን እንደምናርፍ ድንገት ተነገረን፡፡ ይሁን ብለን ተቀብለን፣ አስራ ሁለቱን ደቂቃ በጉጉት ስንጠባበቅ ደግሞ፣ ለተጨማሪ አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ጊዜ በረራው ቀጠለ፡፡ በዚያ ላይ በረራው ጤነኛ አልነበረም፡፡ አንዴ የሚፈጥን፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚረጋጋ ምቾት የማይሰጥ በረራ ነበር፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለ ተሳፋሪ፣ የትም ቢሆን ማረፍን እንጂ፣ማረፊያ ቦታውን አይመርጥም፡፡ እኔም ሆንኩ ሌሎች ተሳፋሪዎች ጉዳዩን ያወቅነው፣ ጠለፋው ከተጠናቀቀና አውሮፕላኑ ጄኔቭ ውስጥ በሰላም ካረፈ በኋላ ዋና አብራሪው ሲነግሩን በመሆኑ እምብዛም አልተደናገጥንም፡፡
ከአውሮፕላኑ ስትወርዱ የነበረው ሁኔታ ምን ይመስላል?
አውሮፕላኑ ጄኔቭ ካረፈ በኋላ በግምት ለአንድ ሰአት ያህል በሩ ሳይከፈት ቆሞ ቆየ፡፡ ዋና አብራሪው ሁሉንም ነገር በግልጽ ከነገሩን በኋላ፣ ከእግር ጣታቸው እስከ ራስ ጸጉራቸው የብረት ጭንብል የለበሱ ሰዎች፣ በሩን በርግደው በፍጥነት ወደ ውስጥ ገቡ። አገባባቸውና መላ ሁኔታቸው አክሽን ፊልም የሚሰሩ ነበር የሚመስሉት፡፡ ሁኔታው እጅግ ያስጨንቅ ነበር፡፡ በመካከል አንደኛው ፖሊስ በእጁ በያዛት አነስተኛ የድምጽ ማጉያ ፈረንሳይኛ በሚመስል እንግሊዝኛ መናገር ጀመረ።
“ዚስ ኢዝ ኤ ፖሊስ ኦፔሬሾን። ዶንት ሙቭ!… ፑት ዩር ሃንድስ ኦን ዩር ሄድ!… ዶንት ሜክ ሙቪ ባይ ሞባይል (በሞባይል አትቅረጹ ማለቱ ነው)” ሲል ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ ሁሉም እጆቹን አናቱ ላይ ጭኖ ድምጹንም አጥፍቶ አቀረቀረ፡፡ ተሳፋሪው በፖሊሶቹ መሪነት አንድ በአንድ ከአውሮፕላኑ እየወረደ፣ ሁለት ሁለት ጊዜ ተበርብሮ ተፈተሸ፡፡
ፍተሻው እንደተጠናቀቀም በትላልቅ ሽንጣም አውቶብሶች እየጫኑ ወደ ተርሚናሉ ወሰዱን፡፡ ተርሚናሉ ላይ ስንደርስ የሚገርም አቀባበል ተደረገልን፡፡ የምንበላው ቁርስና ሻይ ቡና እንዲሁም ለብርዱ ብርድልብስ ተዘጋጅቶ ጠበቀን፡፡ የህክምና ባለሙያዎችና የስነልቦና ባለሙያዎች እርዳታ ሊሰጡን እየተጠባበቁ ነበር፡፡ አስገራሚ አቀባበል ነው የተደረገልን።
ኢትዮጵያውያንስ አላገኛችሁም?
ተርሚናሉ ዉስጥ ገብተን ትንሽ እንደቆየን አንድ ኢትዮጵያዊ ወደ እኛ ሲመጣ ተመለከትን፡፡ ለጊዜው ስሙ ትዝ አይለኝም። ከኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደመጣ ነገረንና ስለሁኔታው ጠየቀን። “አይዟችሁ!… ደርሰንላችኋል!…” የሚል መንፈስ ያለው ማበረታቻ ሰጠን፡፡ ከዚያም የግል ሞባይሉን ከኪሱ አውጥቶ አገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻችን ጋ ደውለን ደህንነታችንን እንድናረጋግጥ ራሱ እየደወለ ያገናኘን ጀመር፡፡
በዚህ ጊዜ ነው፣ በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የመጡት፡፡ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበርን ኢትዮጵያውያንን አነጋግረው አረጋጉን፡፡ በስተመጨረሻም ከተርሚናሉ እንዲወጡ ስለታዘዙ የማስታወሻ ፎቶግራፍ አብረውን ተነሱና ጉዳያችንን በቅርብ እንደሚከታተሉ ነግረውን አበረታቱንና ሄዱ፡፡ ሌሎች ሁለት የኤምባሲው ባልደረቦችም፣የሚፈቀድላቸው ቦታዎች ላይ ሁሉ እየተገኙ ድጋፍ በማድረግ እስከመጨረሻው አብረዉን ነበሩ።
በእለቱ ስለተከሰተው ሁኔታ ምን ትላለህ?
እናቴ እንደነገረችኝ፣ በህፃንነቴ የወራት ዕድሜ ላይ እያለሁ፣ የሆነ ቀን ከታላቅ ወንድሜ መላኩ ገብሬ ጋር ከጎማ ላስቲክ የተሰራ አልጋ ላይ ተኝቼ ነበር። ቡና ስታፈላ ምንጊዜም ዕጣን ማጨስ እማትዘነጋው እናታችን፣ ያጨሰችዉን እጣን እኛ የተኛንበት አልጋ አጠገብ አስቀምጣው ኖሮ፣ እሷ ጎረቤት ደርሳ ስትመለስ ቤቱ በጭስ ተሸፍኖ ጨልሞ ጠበቃት። ጩኸቷን ለቀቀችው። ጩኸት ሰምቶ የመጣ ጎረቤት ነው አሉ ፈልጎ አግኝቶኝ በመስኮት ወደ ውጭ የወረወረኝ። ምህረቱ የተባልኩትም በዚያ ምክንያት ነው። እንዳጋጣሚ እሳቱ ቀድሞ የተያያዘው ወንድሜ በተኛበት በኩል ስለነበር እሱን ማትረፍ አልተቻለም።
የፈጣሪ ምህረት ዛሬም አልተለየኝም፡፡ በአውሮፕላኑ ላይ ሊደርስ ከሚችለው አሰቃቂ አደጋ አትርፎኛል። እንደትላንትናው ሁሉ ነገዬም በፈጣሪ እጅ እንደሆነች አምናለሁ። እርሱ ይሁን ያለው ሁሉ መልካም ነው። ቸርነቱ አይለየኝና ፍቃዱ ሆኖ ለነገ ካበቃኝ ለልጆቼ የምነግረው ተጨማሪ ታሪክ አግኝቻለሁ።
ደህና ነኝ እንኳን ብላት የማታምነኝ እናቴ ብርሃነማርያም ኪአን፣ እጮኛዬ ዮዲት ቦርሳሞን፣ ወንድሞቼን፣ ብቸኛዋን እህቴን፣ አክስቶቼን ከነቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቼን፣ስለደህንነቴ የሚጨነቁልኝን ሁሉ ደህና መሆኔን ንገርልኝ። ከሁሉ አስቀድሞ ስለሆነውም ስለሚሆነዉም ክብር ሁሉ የእርሱ ነውና ፈጣሪ የሚገባዉን ክብር እና ምስጋና ይውሰድ።

Thursday 20 February 2014

(የማለዳ ወግ ... በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ ወዴት እየሔድን ነው ?) በነብዩ ሲራክ


ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች እየሆነ ያለው እና ስማችን የመክፋቱ ነገር ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች በግድያው ማዘናቸውን በመግለጽ በርካታ መልዕክቶችን ልከውልኛል። በጭካኔ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት ዘልቆ ነፍሱን አስጨንቆ ያሳዘነው አንድ ወንድም የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል ....

" ጩኸት ሰሚ ሲያጣ እንዴት ያናዳል ... ሀበሻ የድሮወቹ የሉም ... ወድ የሆነውን የሰውን ደም በከንቱ የሚጠጡ እርኩስ መንፈስ የተጠናውታቸው ውሾች ናቸው .so ሰሞኑን በ ጅዳ አካባቢ ሸር ሄራ አካባቢ የተደረገውን ግፍ ልንገርክ ...በሀበሾች ጭካኔ የተገደለውን ልጅ በአካል አውቀዋለሁ አብዱ ሁሴን ይማም ይባላል ... በሳንጃ ገደሉት ! ልብ በል ... የሳውድ መንግስት ታዲያ እንዴት አያሳድደን ! እንደነዚህ አይነት እርኩሶች እያሉ እኛ ቤተሰብ እንዴት እንርዳ? ልጅስ እንዴት እናስተምር? ..ነብዩ ሰው እንዴት ...የሰውን ነፍስ ያጠፋል? ደግሞም ሳውዲ ውስጥ ? ከተሰራ ለሚገኝ ገንዘብ እጅግ ያሳዝናል ይጎመዝዛል ! ጌታ እውነቱን ይፍረድ ለሀበሻ ጩኸት በቃኝ እኔም ሀበሻ ነኝ!!! " ይላል ! 

ሰሞኑን "ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ ላይ በግፍ የግድያ ወንጀል ተፈጸመ !" የሚለው ወሬ ከጓዳ እስከ አደባባይ ሲናኝ አስከፊውን ሂደት የታዘቡ ወገኖች ኢትዮጵያውያን ብቻ አልነበሩም። ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁና ከሚከታተሉ የሃገሩ ሰዎችም መልዕክቶችና አስተያየቶች ደርሰውኝ በሃፍረትም ቢሆን ለማስተናገድ ተገድጀም ነበር ... የሟችን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱና ስለኢትዮጵያ የሚጽፉ ፣ አንድ ከፍ ያለ ሃላፊነት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያና ሃያሲ የሃገሩ ሰው አዝነውብን አግኝቻቸዋለሁ ። በቁም ነገር በቢሯች አስጠርተው ያሉኝ እንዲህ ነበር " ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ምንድ ነው እንዲህ የመሰለ የዘቀጠ በሃበሾች ያልተለመደ ጉዳይ ተደጋገመሳ ? ሀበሾች ምን ገባባችሁ? ከአመታት በፊት በሪያድ መንፉሃ ፣ ከወራት በፊት በመዲና በአብሃ እና በዙሪያው ያን ሰሞን ደግሞ በኪሎ ተማንያ እና በዙሪያው በሃበሾች መካከል መጨካከን የተሞላበት ድርጊት ታይቷል። ከሁሉም የሚያሳዝነው የግድያ ምክንያቶቹ ጊዜያዊ ጸብን ፣ ጥቅምንና ጥቃቅን የሰው ህይዎትን በጭካኔ ሊያስጠፉ የማይገባቸው ምክንያቶች ናቸው ። ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? " ሲሉ በጥያቄ ላፋጠጡኝ ሳውዲ ወዳጀ የሚሆን መልስ ግን አልነበረኝም ! ብቻ የሆነው አሳዝኖ ፣ አሳፍሮ አንገቴን አሰበረኝ ...

እርግጥ ነው ፣ ባሳለፍናቸው አመታት በሪያድ መንፉአ አካባቢ አልፎ አልፎም በኢትዮጵያውያኑ መካከል በሚፈጠር ግጭት ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ዜጎች በሰላ ጩቤ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞባቸው የመቁሰልና የመገደል አደጋ ምክንያት እንደ ነበር የአይን እማኞች አጫውተውኝ ነበር ። በጩቤ ለመወጋጋቱ ዋንኛ ምክንያትም ደግሞ ተራ ከገንዘብና ከሴት ጋር የተያያዙ እዚህ ግቡ የማይባሉ መሆናቸው ማጤንና መገንዘብ ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል ...በቀደሙት ጥቂት አመታት በሳውዲና የመን ድንበር ከተሞች ይህ መሰሉ ወንጀል የከፋ እንደ ነበር አውቃለሁ። በተለይም በጀዛን ፣ በአብሃና በከሚስ ምሽት በሚባሉ አካባቢዎች በዙሪያው ባሉ የከተማና የገጠር ከተሞች በከተሙ ኢትዮጵያውያን መካከል ተፈጸሞ የምንሰማው ግድያ ፍጹም ጭካኔ ያልተለየው መሆኑ ይጠቀሳል ! ወደ አብሃና ከሚስ ምሸት ለስራ ባቀናሁባቸው ቀናት በእኛ ዙሪያ እየሆነ ያለውን ለመስማት የከበደ መረጃ በእጀ መድረሱን አስታውሳለሁ። በህገ ወጥ መንገድ ዜጎቻችን ከየመን ሳውዲ በሚያመላልሱ ለገንዘብ በገንዘብ እየሸጡ የሚተዳደሩ ደላሎችና አቀባባዮች በጎሳ ተቧድነውና ብሔርን ለይተው የሚከሰተውን ግጭት ከጩቤ ያለፈ እንደ ነበርም በቦታው ተገኝቸ ታዝቤያለሁ። በተለይም በአብሃ አካባቢ በግጭቱ ስለተቀጠፈው ህይዎት ፣ ፍርድን ይጠባበቁ ስለነበሩ የእኛ ገዳዮችም የፍርድ ሂደት በቅርብ እከታተል ነበር ። ከሁሉም የሚያሳዝነው የሰውን ልጅ ያህል ታላቅ ፍጡር በስለት የሚጠፋበትን ምክንያት መስማት እንደ ነበርም ትዝ ይለኛል። ከሃገር ቤት ያለ የዘር ፣ የግል ጥላቻና ጸብን መሰረት ያደረገው የደም መቃባት ፣ በገንዘብ መካካድ " ጓደኛየን ነጠቀኝ!" ፣ "የሰማንያ ሚስቴን ደፈረ !"፣ በሚሉትና በመሳሰሉት ክሶች የሚያጠነጥነው ብቀላ በፍትህ ሳይሆን በጭካኔ ለመወጣት የሚፈጸም ያረጀ ያፈጀ ይትበሃል ሳውዲ ተከትሎን መጥቶ ስማችን ማርከሱ ደግሞ ከሁሉም በላይ ያማል !

በያዝነው አመት ከጅዳ በ400 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው በሙስሊማን ቅዱስ ከተማ በመዲናም በዜጎቻች መካከል በተፈጠረ የቨዛ ሽያጭ እና ተጓዳኝ የገንዘብ መካካድ ያስከተለው አምባጓሮ በቅዱሷ ከተማ ቅዱስ የማይባል ግድያ ለመፈጸሙ ምክንያት ነበር ። ይህም የጭካኔ ወንጀል የተፈጸመበት ኢትዮጵያዊ ፣ ወንጀል ፈጻሚው ኢትዮጵያዊው መሆኑ ደግሞ ጉድ አሰኝቶ አሳፍሮን አልፏል። ከወራት በፊትም እዚሁ ጅዳ በተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያውያን መካከል የተነሱ አምባጓሮዎች በተመሳሳይ ጭካኔ በተሞላባቸው የግድያ ድርጊቶች የተከበቡ ወንጀሎች ምክንያት ነበሩ ማለት ይቻላል። እናም ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል ....

ባሳለፍነው ሳምንት በጭካኔ የተገደለው ወንድም ወንጀል ተጠርጣሪ ፣ ተጠያቂ የቅርብ ጓደኛ ወዳጁ እንደነበረና ከቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ሰማን ! አብዱ በማጣታቸው ትልቁ የሃዘን መርግ የወደቀባቸው፣ የሚይዙት የሚጨብጡ ያጡት ፣ ቤታቸው የጨለመባቸው አንዲት ሴት ልጂና የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱ ሃዘን የከበደ ነው...ስለአብዱን ቅንነት፣ ሰው አማኝ ፣ ትጉህና ታታሪነቱን የሚመሰክሩት ባልንጀሮቹም ሃዘናቸው መሪር ያደረገው የተፈጸመው የጭካኔ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ቀዳሚ ተጠርጣሪ የቅርብ ወዳኛ መሆኑ ነበር ። በዚህም ሊያምኑት በከበደ ድርጊት እርር ድብን ብለው አዝነዋል! ዛሬ የማይሰማ የማያየን አብዱ ሁሴን በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል ይገኝ እንደነበር በቅርብ ጓኞቹ ጨምረው አጫውተውኛል ። የወንድም አብዱ ሁሴን ይማም የቀብር ስነ-ስርዓት ትናንት የካቲት 12 / 2006 ረቡዕ ከቀትር በኋላ በጅዳ ከተማ ተፈጽሟል ! አብዱ የሔደው ሁላችንም ወደ ማንቀርበት የላይኛው ቤት ነው ! ነፍሱን ይማረው ! " አላህ ይርሃሙ !"

ወንጀሉን በትኩሱ ለማቅረብ በፖሊስ ክትትክ መሆኑና ተጠርጣሪ ወንጀለኛው ባለመያዙ የማለዳ ወጌን እንዳዘገየው ቢያስገድደኝም መረጃውን ባሳለፍናቸው ቀናት ከበርካታ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ሞክሬ ነበር ። በዚህ መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ዙሪያ እየተነጋገረ የሚገኘውን አብዛኛው የጅዳ ነዋሪ " ህጋዊ ህገ ወጥ " ነገን ምን ይከተል ይሆን እያለ በጭንቀት በሰቀቀን እየጠበቀ ባለበት ሰአት የዚህ መሰሉ ድርጊት መፈጸም " እንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ !" ሆኖበት ተመልክቻለሁ! ለእኔም የሆነብኝ እንዲያ ነው ...

ድርጊቱ አሳዝኖኝ ለማውገዝ ያነሳሁት ብዕር መቋጫ የሚሆነው ሳውዲው ሃያሲ ወዳጀ ያጫወቱኝን ዘልቆ የሚሰማ ያልመለስኩት ጥያቄ ነው ። ሃያሲው ሃበሾች በዚህ መሰል ድርጊት እንደማንታወቅ ተናትነው ከቅርብ አመታት የሰበሰቧቸው መረጃዎች ቢያሳስቧቸው ቆጣ ብለው በንዴት ሲያጠይቁ "ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? " ነበር ያሉኝ ...እኔም ተጠርተን የማናውቅበት ወንጀል ሲደጋገም አሞኛልና ድርጊቱን አወግዘዋለሁ! ወደ መጨረሻም አሳፍሮ መልስ ያጣሁለትን የሃያሲውን ወዳጀ ጥያቄ ላጠይቅ ግድ አለኝ ... ግንስ ... በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ እየተጠላላን ወዴት እየሔድን ነው ? ምንድን ነው እየሆነ ያለው? 

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

Israel Begins Deporting African Asylum Seekers to Uganda


Mideast Israel African Migrants
In this Sunday, Jan. 5, 2014 file photo, African migrants chant slogans during a protest in Rabin’s square in Tel Aviv, Israel. Dozens of Africans have accepted an Israeli government offer to relocate to Uganda, an Israeli official said Wednesday, part of the Jewish state’s efforts to cope with an influx of migrants from the continent. (AP Photo/Ariel Schalit, File)
February 20, 2014 (Mint Press News) — The secret program, meant to lower the number of African immigrants flocking to the country for a better life, reportedly includes a $3,500 cashincentive to each deportee.
Due to intense pressure by the Israeli governmentand harsh living conditions, immigrants seeking asylum from several African nations have agreed to leave the state of Israel and relocate to a third-party country on the African continent, according to various reports.
Over the last several weeks, dozens of asylum seekers have agreed to leave Israel for Uganda, and some have already left, the Israeli newspaper Haaretz reported on Wednesday.
“Haaretz has obtained information that a Sudanese citizen who had been detained at the Saharonim detention center flew to Uganda, where he was reunited with his family,” the newspaper reported.
“The man called his friends in Israel and said there were six other asylum seekers from Sudan with him on the flight, all of whom had been released from Saharonim. The man also said he had received a grant of $3,500 for leaving the country, which is in keeping with the government’s ‘voluntary departure’ procedure.”
Saharonim Prison is an Israeli detention facility for African asylum seekers — mostly from Sudan, Eritrea and Ethiopia — located in the Negev Desert.
The Africans claim they are fleeing persecution and danger. Israeli officials claim they are job seekers, but have had a difficult time deporting them because of grave human rights situations in their home countries, which are also often in some state of conflict or post-conflict status.
Another report by the Associated Press sourced an unnamed Israeli official who confirmed the existence of the program and said about 30 African immigrants have so far agreed to leave Israel for Uganda.
Israeli officials told the High Court of Justice in June that it had reached a deal with a third country that could take in the immigrants, but would not reveal the name of the country, Haaretz reported. Senior Israeli officials later confirmed that the country was Uganda.
Both the Haaretz and AP articles reported that Ugandan officials have denied the existence of theprogram.
“We are not privy to such an arrangement,” David Kazungu, a Ugandan government commissioner who is in charge of refugees, told the AP.
The East African nation has played host to many refugees through the years, especially those emigrating from conflict-wracked countries along its borders, like the Democratic Republic of the Congo and South Sudan. However, in this instance it appears there are no guarantees that once the immigrants arrive in Uganda they would be afforded protection or asylum status.
“The State of Israel is proposing to asylum seekers a return to Uganda with no assurances or official agreement,” Reut Michaeli, director of the Hotline for Refugees and Migrants, said on Wednesday, according to Haaretz.
“In addition to all that, it is known that Uganda deports asylum seekers to their countries of origin.”
The report further notes that as far as Michaeli understood the situation, the asylum seekers will not receive legal status in Uganda and they will not have any papers allowing them to leave if they wanted to go anywhere else on their own.
According to the Population and Immigration Authority, as of Sept. 2013 there were 53,646 asylum seekers from Africa in Israel. Among them were 35,987 Eritreans, 13,249 Sudanese and 4,400 people from other countries, Haaretz reported.
Source: Mint Press News